




በተቋሙ እስካሁን 218 ቴክኖሎጂዎችና እና መረጃዎችን በሰብል፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በእንስሳት እርባታ ማላመድና ማፍለቅ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 123 ቴክኖሎጂዎችን በማሸጋገር ለተጠቃሚ አርሶና አርብቶ አደሮች ማድረስ መቻሉን ተነግሯል።
ኢንስቲትዩት በቦንጋ ከተማ ባዘጋጀው አመታዊ የምርምር ስራዎች ኮንፈረንስ ላይ በሰብል፣ በተፈጥሮ ሀብት እና በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የተሰሩ የምርምር ውጤት ኢግዚቢሽን ለዕይታ አብቅቷል።
የኮንፈረንሱ ታዳሚዎች በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች የተሰሩ የምርምር ውጤቶችን እየጎበኙ ይገኛሉ ።
በዕድገቱ በዛብህ
