የናይጄሪያ ወታደራዊ ልዑክ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የለውጥ ሥራዎችን ጎበኘ

Spread the love

የናይጄሪያ ወታደራዊ ሪሶርስ ማዕከል ልዑካን ቡድን አባላት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የለውጥ ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም፤ ዘመናዊ የፖሊስ መገናኛ ዲጂታል ሬድዮ፣ የኮማንድ ኮንትሮል ማዕከልን፣ የቀጥታ ጥቆማ መቀበያ፣ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያና ዘመናዊ ካሜራና የደኅንነት መሣሪያ የተገጠመላቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎችን ተመልክተዋል፡፡

የተቋሙን ተልዕኮ፣ አደረጃጀት፣ እሴቶችና ዓላማ በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ዋና መምሪያ ተጠባባቂ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ደጀኔ በቀለ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላትም በጉብኝታቸው ባዩት ነገር መደሰታችውን ገልጸው፤ ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ምሥጋና ማቅረባቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *