




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የክልል ሴክተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ በቴፒ ከተማ አካሂዷል።
በአባላት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ቴፒ ብዝሃ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ደምሴ ደንቦ የፓርቲውን አሰራሮች እና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጉላት ተግባራትን የመምራት ሂደት የተሰራበት አግባብ የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።
በፓርቲው እሳቤ የተሰሩ ተግባራት አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ተናረው ለቀጣይ ተልዕኮ የተቀናጀ ተግባር ለማከናወን ወንድማማችነትን እህተማማችነትን ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።
የፖለቲካ ግንባታ የሁሉም የብልጽግና ቤተሰብ ቅንጅትና ህብረት ነው ያሉት አቶ ደምሴ ጥንካሬዎችን እያጎሉና ጉድለቶችን እያረሙ ለህዝብ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መስራት አለብን ብለዋል።
እንደ ብዝሃ ማዕከል ለህዝብ ተጠቃሚነት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናመኑን የገለጹት ኃላፊው ለዚህም ስኬት የሁሉም አባሉና አመራር ቅንጅትና አንድነት የጎላ መሆኑን ተናግረዋል ።
የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት አባል ወይዘሮ ገነት መኩርያ በአባላት ኮንፈረንስ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በየተዋረዱ ያሉ ተቋማት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ፈጽመው የተሻለ የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲኖር ግንባር ቀደም የብልጽግና አባላት ለተግባር ስኬት ዝግጁ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በፓርቲው ልዩ ትኩረት ከተሰጠባቸው ዘርፎች ዋናዎቹ ሰው ተኮር ተግባራት መሆኑን የገለጹት ወሮ ገነት የአቅመ ደካማና አረጋዊያንን ጨምሮ የደሀ ደሀ ቤት ግንባታና ማዕድ ማጋራት ተግባራት በሁሉም አደረጃጀቶች የተሻለ አፈፃፀም እየታየ መምጣቱን ተናግረዋል።
በፓርቲው መሪነት የተገኙና የተሻሻሉ አፈፃፀሞች በማጠናከር የተሰሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋትና በመቀመር አፈጻጸሞችን አጠናክሮ ማስቀጠል በቀጣይ በጀት ዓመት የተሻለ መሰራት እንዳለበት አንስቷል።
የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የክልል ሴክተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በፓርቲው መሪነት እየተሰሩ ያሉ ተግባራት የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን ተናግረው ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችል በርካታ ተግባራት የተከናወኑ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የፓርቲ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የውስጠ ፓርቲ አንድነት አስተሳስሮ የመምራት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተመላክቷል ።
ለብልፅግና እሳቤ ግብ መምታት አንዱ ማነቆ ብልሹ አሰራሮች በመሆኑ ይህን ለመከላከል የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ሁሉም አባልና አመራር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በየጊዜው የሚከሰቱ የዋጋ ጭማሪና የኑሮ ውደነትን ለመከላከል በፓርቲው እሳቤ የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ተግባራዊ እንዲሆን በጋራ መተጋገዝ ይኖርብናል ነው ያሉት።
ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተጀመረው የብልጽግና እሳቤ ከግብ እንዲደርስ የሁሉ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።
በአባላት ኮንፈረንስ ላይ የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የክልል ሴክተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል።
