የብራዚል አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ መሥራት እንደሚፈልግ ገለፀ

Spread the love

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ የብራዚል ምክትል አምባሳደር ጃክሰን ሊማን ጨምሮ ኢምብሬር የተባለው የሀገሪቱ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የስራ ኃላፊዎችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

መንግሥት ለአቪዬሽን ዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ጋር በማገናኘት የአህጉሪቱ ኩራት ሆኖ እንዲዘልቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በአቪዬሽን ዘርፍ የተሰማሩ በርካታ የግል ኦፕሬተሮች መኖራቸውን ጠቁመው፤ የውጭ ባለሃብቶች ጭምር ሊሳተፉ የሚችሉባቸው አዋጭ የሆኑ የኢንቨስትመንት አማራጮች መለየታቸውን አክለዋል።

የአውሮፕላን ጥገና እና የአውሮፕላን አካል የማምረት አማራጮች አዋጭ የሆኑ ዘርፎች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ለአብነት ማንሳታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኩባንያው ተወካዮች በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለአቪዬሽን የሰጠችውን ትኩረት በመመልከት በተለያዩ ዘርፎች መሰማራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

የአውሮፕላን ጥገና፣ የአውሮፕላን አካላት ምርትና የስልጠና መስኮች ቀዳሚ የትብብር ፍላጎቶቻቸው እንደሆኑ በማብራሪያቸው አንስተዋል።

በተጨማሪም ለሀገር ውስጥ በረራ የሚያገለግሉትን አውሮፕላኖችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፍላጎት ባሟላ መልኩ ማቅረብ እንደሚችሉና ከአየር መንገዱ ጋርም በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ አንስተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *