በኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ የተራቆቱ ቦታዎች ወደነበሩበት እንዲመለሱ እየተሠራ ነው

Spread the love

በኮይሻ የውኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ የተራቆቱ ቦታዎችን ቀድሞ ወደነበሩበት ተፈጥሯዊ ይዞታ የመመለስ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በፕሮጀክቱ የአካባቢያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ዕቅድ ሥራ አስኪያጅ ግዛቸው ደሳለኝ እንደገለፁት፤ ለፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ ግብዓት የተቆፈሩ እና ተረፈ ምርቶች ተጠራቅመውባቸው የነበሩ ቦታዎችን ወደ ተፈጥሯዊ ይዞታቸው የመመለስ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡

በዚህም ፕሮጀክቱ ራሱን የቻለ የሥራ ቡድን እና የችግኝ ጣቢያ አቋቁሞ ከግንባታ ሥራው ጎን ለጎን የመልሶ ማልማት ሥራ እያከናወነ ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልመረጃ አመላክቷል፡፡

የተለያዩ ማሽነሪዎችና ወርክ ሾፖች የተተከሉበት ቦታን ጨምሮ በፕሮጀክቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች ቀሪ ቦታዎችን ወደ ነበሩበት የመመለሱ ሥራ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

የመልሶ ማልማት ሥራው የአካባቢውን ሥነ-ምኅዳር ለመጠበቅ ብሎም በቀጣይ የሚኖረው ሰው ሠራሽ ኃይቅ በደለል እንዳይሞላ በማድረግ ግድቡ የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችላል ማለታቸዉን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *