







የአስተዳደር ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የአባላት ኮንፈረንስ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ ብልጽግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህታማማችነትን መሠረት ያደረገ ገዢ ትሪክት ለመገንባት እየሰራ ያለው ዘመን ተሻጋሪ ፓርቲ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የህዝብና የአባላት የተደራጀና የተቀናጀ ተሳትፎ ለሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡
የቦንጋ ማዕከል የክልል ተቋማት የአስተዳደር ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት አባላት የፓርቲያችንን ፕሮግራም፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ መመሪያዎችን በየጊዜው የሚቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች በተገቢው በመገንዘብ ለወጤታማነት መታገል የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
የቦንጋ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ በዚህ ኮንፈረንስ የሚቀርበውን የህብረቱ አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የጋራ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የሚጠናቀቅ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡
ፓርቲው ብልጽግና ትላንትን መነሻ አድርጎ ዛሬ ላይ በመሆን ነገን መዳረሻ በማድረግ እንደሀገር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
እንደ ቦንጋ ማዕከል አስተዳደር ዘርፍ ለህዝብ ተጠቃሚነት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወኑን የገለጹት አቶ ሳምሶን ለዚህም ስኬት የሁሉም አባሉና አመራር ቅንጅትና አንድነት የጎላ መሆኑን ተናግረዋል ።
በተከተል ወ/ሚካኤል
