የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ይካሄዳል

Spread the love

የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) የሰላም አስከባሪ ኃይል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሀገራት አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ በዩጋንዳ ይካሄዳል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ኢንቴቤ ገብተዋል።

በአፍሪካ በተለይም የሶማሊያ ጎረቤት ሀገራት በሀገሪቷ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ትልቅ ዋጋ መክፈላቸውን ኢጋድ ገልጿል።

የተከፈለው ዋጋ ሰላሟ የተጠበቀ ሶማሊያ እንድትኖር ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን አመልክቷል።

የሶማሊያ ሰላም ለዓለም መረጋጋት ቁልፍ ምሰሶ መሆኑንም ነው ኢጋድ ያስታወቀው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *