በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 227 ሄክታር ማልማት የሚችሉ 11 የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት አፈፃፀም ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተርኢንጂነር አሸናፊ ሽብሬ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አክለዋል።

በክልሉ መንግሥት በጀትና ዘርፉን በሚደግፉ በተለያዩ ፕሮግራሞች የበጀት ድጋፍ በርካታ የመስኖ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንዳለ የገለጹት ዋና ዳይሬክትሩ ከእነዚህ ተግባራት መካከል የመስኖና ድሬኔጅ ሲስተም ጥናትና ዲዛይን ሥራ አንዱ ሲሆን በ2017 የበጀት ዓመት 27 ሺህ 640 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ የ23 መስኖ ፕሮጀክቶች (የ20 አነስተኛ እና የ3 መካከለኛ ፕሮጀክቶች) የጥናትና ዲዛይን ሥራ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በዚህም በ2017 የበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ላይ 2 ሺህ 77 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ የስድስት መስኖ ፕሮጀክቶች (የአምስት አነስተኛ እና የአንድ መካከለኛ ፕሮክቶች) የጥናትና ዲዛይን ሥራ ተጠናቆ ለግንባታ ዝግጁ መደረጉን ኢንጂነር አሸናፊ ሽብሬ ተናግረዋል፡፡

በመስኖ አውታሮች ግንባታ ረገድም በክልል ደረጃ 1ሺህ 227 ሄክታር መሬት በማልማት 2 ሺህ 829 ቤተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ11 አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው ያሉት ኢንጂነር አሸናፊ ሽብሬ በወረዳ ደረጃም በተመሣሣይ መልኩ 247.6 ሄክታር መሬት በማለማት 474 ቤተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የ18 መስኖ አውታሮች ግንባታ በሂደት ላይ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ከእነዚህም መካከል በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ላይ 405.06 ሄክታር መሬት የሚያለሙ የ7 አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቆ ለልማት እንደሚውልም ተናግረዋል፡፡

ነባር የመስኖ ተቋማትን ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና ለመደበኛ መስኖ ልማት ዝግጁ ከማድረግ አኳያ በበጀት ዓመቱ በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ 93 ነባር መስኖ ተቋማት መካከል 3 ሺህ 641 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ 78 የመስኖ ተቋማትን በየደረጃው ካለው ከሴክተሩ መዋቅር፣ ከባለድርሻ አካላትና ከመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ጋር በመቀናጀት ወደ ልማት ማስገባት የተቻለ መሆኑን ያብራሩት ዋና ዳይሬክተሩ 706 ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችሉ የ13 ነባር መስኖ ተቋማት ጥገናና መልሶ ግንባታ ሥራ በምግብ ሥረዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በተለያዩ ወረዳዎች እየተከናወነ እንዳለ አስረድተዋል፡፡

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *