




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሰዒድ ኢብራሂም ባደረገው ንግግር፣በኢኮኖሚ ዘርፍ ወጣቶች ቁጠባን ባህል አድርገው ውጤታማ በሚሆኑባቸው ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ለማድረግ የተሻለ እንቅስቃሴ መደረጉን ገልጿል ።
ወጣቶች የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት መደረጉን ጠቅሰው በተለይ ወጣቱን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማስገባት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በማመቻቸት ላይ እንገኛለን ብሏል።
ወጣቶች በፖለቲካውም ዘርፍ ብቁ፣ በራስ የሚተማመን እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ወጣት አመራር መሆን እንዳለባቸውም መክረዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ በክረምትና በበጋ ወራት የበጎ ተግባራትን ግንባር ቀደም ሆነው በመሳተፍና በማስተባበር ስለተከናወኑት ተግባራት አመስግነው በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥል አስታውቋል ።
በመድረኩ የክልሉ ወጣቶች ክንፍ ምክር ቤት አባላት ፣የክልል ስራ አስፈጻሚዎች ፣የዞን ፣ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር የወጣቶች ክንፍ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
በካሳሁን አሰፋ
