ለአመታት ተቋርጦ የነበረው የዲሪ ማሻ አስፋልት መንገድ ስራ እንደገና ሊጀመር ነው ።

Spread the love

ለአመታት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የሰነበተው የዲሪ_ማሻ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ እንደገና ወደ ስራ የማስገባት ስነስርዓት በካፋ ዞን ጊንቦ ወረዳ ይደረጋል።

ይህንን ስነ _ስርዓት ለማስጀመር የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ አየለ የተገኙ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ወደ ስፍራው ሲደርሱ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የካፋዞን አመራሮችና የጊንቦ ወረዳ ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *