3ኛ ዙር የኢትዮጵያ ታምርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተከፈተ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮዉ የተዘጋጀዉ 3ኛው ዙር ክልል አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በሚዛን አማን ተከፍቷል ።

አምራች ኢንዱስትሪው ኢኮኖሚያዊ ብዝሃነትንና ዕድገትን በማጎልበት ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ ወሳኝ ነው።

ዘመናዊ ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ያለውም ከ1945 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑን ታሪክ ያስረዳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ያለው ዕድገት ያልተስተካከለ በመሆኑ በማኑፋክቸሪንግ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ፣የምርት ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ ፣የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ኢንቨስትመንት ለመሳብና ዕድገትን ለማጎልበት የተጀመረው ክልል አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኢኒሼቲቭ ዘንድሮ ለ3ኛ ዙር እየተካሄደ ይገኛል።

በክልሉ በአነስተኛ 602፣በመካከለኛ 135፣በከፍተኛ 10 በጠቅላላው 747 ኢንዱስትሪዎች ያሉ ሲሆን በዘርፎች ደረጃ በእንጨትና ብረታብረት 305 ፣በጨርቃጨርቅ 251፣በአግሮ ፕሮሰሲንግ 155፣በቆዳና ቆዳ ውጤቶች 7 እንዲሁም በኬሚካልና አምራች ኢንዱስትሪዎች 29 መኖራቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ በአምራች ኢንዱስትሪው የተለያዩ ምርቶች ቀርበዋል።

በዚሁ ኤግዚቢሽን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣የዞን አመራሮችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *