




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የየዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 ዓ.ም የ9 ወር የአስፈፃሚ አካላት ዕቅድ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ ገምግሟል ።
በግምገማዉ መድረኩ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በአስፈፃሚ ተቋማት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወነው ስራዎችን ቋሚ ኮሚቴዎቹ ስከታተሉ መቆየታቸው ተጠቁሟል ።
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤና የማህበራዊ ዘርፍ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ፀሀይ ደርጫ ምክር ቤት ትልቁ የፖለቲካ ስልጠን ባለቤትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዋናኛ ተቋም መሆኑን አንስተው በክልሉ ባለፉት 9 ወራት በማህበራዊ ዘርፍ የተከናወኑት ተግባራት መሻሻል መታየታቸው ገልጸዋል ።
ምክትል አፈጉባኤዋ በማህበራዊ ዘርፍ በተለይ በጤናው፣ የወባ ስርጭት ለመቀነስ መከላከልን መሠረት ያደረጉ ተግባር መሠራታቸውን እንዲሁም የመድኃኒት አቅርቦትን መጠንን ማሳደግ ጨምሮ ሌሎች በማህበራዊ ዘርፍ የተተገበሩት ለአብነት አንስተዋል ።
ከትምህርት ዘርፍ አንፃርም የመማር ማስተመር ተግባር እየተመራ ያለበት ሁኔታ፣ ለክልላዊና ሀገራዊ ፈተና ለሚዘጋጁ ተማሪዎች በየዞኖቹ ሚቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር እየተሰጡ ያሉ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ትምህርት፣ የቅድመ አንደኛ ተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም ጅምር ስራዎች ስለመሆኑ አንስተው ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አዲስምዕራፍ አለሙ፣ በክልሉ በግብርናው ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች አስፍቶ በማረስ ምርትን ከማሳደግ አንፃር አመርቂ ዉጤት የተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
በተለይ በፍራፍሬና ሆርቲካልቸር፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ለችግኝ ተካላ የሚሆን ዘር ዝግጅትና ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች የጽድቀት መጠን ከማሻሻል፣ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ሌሎች ተግባራት ትኩረት ከተሰጡት መካከል መሆናቸው አቶ አዲስምዕራፍ ጠቁመዋል ።
በክልሉ ፍርድ ቤት አካባቢ ከዚህ ቀደም ሲል ዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ተዘዋዋሪ ችሎት ጋር ተያይዞ በርካታ መሻሻሎች እየተደረጉ ፊትህን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉት ጥረቶች አበረታች መሆኑን የሚናገሩት ደግሞ የክልሉ ህግ፣ ፊትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አምሳለ ንጋቱ ናቸው ።
ሌለኛው ጥሩ አፈፃፀም የታየበት ጸጥታን ለመስፈን የተሰራ ስራ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የክልሉ ህግ፣ ፊትህና መልካም አስተዳደር የሚመለከቱ ተግባር እንዲሻሻል ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ጋር የተጀመሩ የጸጥታ እና የሃሳተኛ ሚዲያዎች የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ አምሳለ አስታውቋል ።
በጀት፣ ፋይናንስ ኦዲት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ የኋላሸት በላይነህ፣ በመንግሥት አስፈፃሚ ተቋማት የሚመደቡ በጀቶች በተገቢው መንገድ ለታለመለት አላማ እንዲዉል የምክር ቤቶች የመከታተል ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
እንደ ክልሉ በጀት፣ ፋይናንስ ኦዲት ዘርፍ አጠቃላይ የክልሉ ተግባራት የሚከናወነው በገንዘብ መሆኑን አንስተው ለዚህም ይህንን ዘርፍ ማጠንከር፣ ማዘመንና ቴክኖሎጂን በመከተል ኦዲት ግኝት ከማስመለስ፣ ግብር ከፋዩን የደረጀ ሽግግርና የግብር ህግና አሰራ በመትከል ከመስራት አንፃር ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም ወ/ሮ የኋላሸት ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ አሰገደች ወ/የስ ፣ ከተማና መሠረተ ልማት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ በተለይም በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ የመንገድ ልማት ዘርፍ ታቅደው የጠጠርና መደበኛ የመንገድ ጥገና ስራዎች በስፋት መከናወናቸውንና አዳዲስ መንገድ ስራ እና የድልድዮች ግንባታ ስራ መሠራታቸውን አንስተዋል፡፡
ከመናኸሪያ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ትርፍ ከመጫንና ከታርፍ በላይ ከማስከፈል ጋር ተያይዞ የሚደረግ ጥረት መኖሩን የገለጹት ወ/ሮ አሰገደች በቀጣይ ስራው ቅንጅታዊ ስራንና ክትትል የሚጠይቅ በመሆኑ የሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የጋራ ስራ ልሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ያልተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ያነሱት ቋሚ ኮሚቴዎቹ በቀጣይም የክትትልና የቀጥጥር ስራ የበለጠ እንደሚጠናከር አስረድተዋል ።
በግምገማ መድረኩ የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።
በተከተል ወ/ሚካኤል
