





በክልሉ ሁሉም ማዕከላት ላይ ባሉ ቢሮዎችና ተቋማት የተደረገው ውይይት የመንግስት ሠራተኞች ወቅታዊ ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በውል በመገንዘብ ለቀጣይ ተልዕኮ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ለመፍጠር ያለመ ነው።
በመድረኮችም “የመሃሉ ዘመን ወጥመድ መሻገር !” በሚል መሪ ሀሳብ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርገውበታል።
በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ የሀገሪቱን ሪፎርም ለመግታት የሚንቀሳቀሱ አካላትን በመለየት ሁሉም ሠራተኛ የማይዋዥቅ ተቋማትን በመፍጠር ሀገራችንን ወደታለመላት እድገት ማሸጋገር እንዳለበትም ተገልፀዋል።
የመንግስት ሰራተኛው የመሀል ዘመን ወጥመድን በጽናት በመሻገር የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን እውን ለማድረግ በትጋት መስራት እንደሚገባ ተጠቁመዋል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
