

























በዚህ አምድ ዛሬ በየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዞኖች አንዱ የሆነውን የዳውሮ ዞንን እንቃኛለን!
የዳውሮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ዞኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዞኑ በ10 ወረዳዎች፣ በ4 ከተማ አስተዳደሮች፣ በ172 የገጠርና 25 የከተማ በድምሩ 197 ቀበሌዎች የተዋቀረ ዞን ነዉ። ዞኑ በስተ ምዕራብ የኮንታ ዞን፣ በስተ ሰሜን የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት የጅማ ዞን፣ በስተ ሰሜን ምስራቅ የሀድያ ዞንና የጣምባሮ ልዩ ወረዳ፣በስተ ምስራቅ የወላይታ ዞን በስተ ደቡብ የጋሞና የጎፋ ዞኖች ያዋስኑታል።
የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ነው። ከተማው ከዞኑ ከተማነት ባሻገር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የህግ አውጪና ማህበራዊ ክላስቴር፣ የታርጫ ዙሪያ እና የታርጫ ከተማ አስተዳደር መቀመጫ በመሆ የምታገለግል ከተማ ናት።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?
በዚህ አምድ ዛሬ በየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ዞኖች አንዱ የሆነውን የዳውሮ ዞንን እንቃኛለን!
የዳውሮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሰት አሰተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ዞኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዞኑ በ10 ወረዳዎች፣ በ4 ከተማ አስተዳደሮች፣ በ172 የገጠርና 25 የከተማ በድምሩ 197 ቀበሌዎች የተዋቀረ ዞን ነዉ። ዞኑ በሰተ ምዕራብ የኮንታ ዞን፤በሰተ ሰሜን የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት የጅማ ዞን፤በስተ ሰሜን ምስራቅ የሀድያ ዞንና የካምባታ ጣምባሮ ዞን፤በሰተ ምስራቅ የወላይታ ዞን በስተ ደቡብ የጋሞና የጎፋ ዞኖች ያዋስኑታል።
የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ነው። ከተማው ከዞኑ ከተማነት ባሻገር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የህግ አውጪና ማህበራዊ ክላስቴር፣ የታርጫ ዙሪያ እና የታርጫ ከተማ አስተዳደር መቀመጫ በመሆ የምታገለግል ከተማ ናት።
የዳውሮ ዞን አጠቃላይ ይዞታ አብዛኛው ዙርያ ገባው በጎጀብና በኦሞ ወንዞች የተከበበ ሲሆን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በምድር ወገብ 6°36-7°21 ሰሜን “ላቲትዩድ” እና ዜሮ ድግር ሎንግትዩድ 36°41-37°53 ነው።
የዞኑ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ ወጣ ገባ ኮረብታማና ተራራማ ስሆን በሀገር በቀል ዛፎች የተዋቡ የአጦ ኮርቻ ቅርጽ ተራራ፣ ኡምቡቲ ተራራ፣ የኢሰራ ተራራ በዋናነት የሚጠቀሱ ሆኖ ሥነ ምህዳሩ 38 በመቶ ቆላማ፤41 በመቶ ወይና ደጋና 21 በመቶ ደጋማ ተብለው በሦስት የአየር ንብረት ቀጠናዎች ይከፈላሉ።
የዞኑ ቆዳ ስፋት 446, 082 ሄክታር ስሆን ከዚህ ውስጥ 63 በመቶ ማልማት የተቻለ፣ 6.81 በመቶ የግጦሽ፣ 21.81 በመቶ በደንና በቁጣቁጦ የተሸፈነ፣በውሃ የተሸፈነ 3.87፣ ሊለማ የማይችል 3.91 እና 0.6 በሌሎች የተሸፈነ ነው።
በዞኑ አጠቃላይ የዓመታዊ ሰብሎች ምርት መጠን በ2011/2012 ዘመን ወደ 11.534.710 የነበረው በ2015/2016 ምርት ዘመን 22.794.935 ኩንታል ከዚህም ጋር በተያያዘ በዓመታዊ እና ቋሚ ሰብል የተሸፈነ በ2011/2012 ምርት ዘመን ከነበረበት 202.160 ሄክታር በ2015/2016 ምርት ዘመን 280.548 ሄክታር ደርሱዋል።
ዞኑ የእንሰት ተክል አብቃይ ከሆኑ አከባቢዎች አንዱ ሲሆን ይህን እድል እንደምቹ ሁኔታ በመጠቀም የእንሰት ተክል ልማትን በማዘመን ከዘርፉ የላቀ ጠቀመታን ለማግኘት በሚያስችል አኳሃን በዞኑ ሥነምህዳር በስፋት ለምተው ይገኛል።
በዞኑ የእንሰት ተክል ለምግብነት ከማዋል ባሻገር የአካባቢውን ስነ ምህዳር ምቹ በማድረግ ለጥምር ደን እርሻም ድምቀት ሆኖ እያገለገለ ያለ ልዩ ተክል ነው።
ከዞኑ ማህበረሰብ የአኗኗርና የአመጋገብ ባህል ጋር ለዘመናት ተቆራኝቶ የቆየው የእንሰት ተክል የጎጆዎች ግርማ ሞገስ፣ የጓሮዎች ማድመቂያና አረንጓዴ ሰገነት ከመሆን ባሻገር ጠቃሜታዎቹ በርካታ ናቸዉ።
የእንሰት ተክል ለሰው ምግብ፣ ለእንስሳት መኖ፣ ለአፈር ለምነት፣ ለአየር ንብረት ሚዛንን ለመጠበቅ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት፣ ለቤት መስርያነት፣ ለመድሃኒትነት፣ ድርቅ እያስከተለብን ያለዉን ፈተና ለመቋቋም ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ስሆን
ከስሩ አንስቶ እስከ ቅጠሉ ድረስ ያሉት መላ ክፍሎቹ የተለያዩ ጥቅሞችን ያበረክታሉ።
የዳውሮ ብሔረሰብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ 13 ነባር ብሔር/ብሔረሰቦች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የዳውሮ ብሔረሰብ ቋንቋ ዳዉሮኛ ይባላል፡፡ ዳዉሮኛ በኦሞቲክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡
የ1999 ዓ.ም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤትን መሠረት በማድረግ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ባደረገው ትንቢያ በ2016 የበጀት ዓመት የዞኑ ህዝብ ብዛት 807,988 (412,144 ወንድ እና 412,144 ሴት) እንደሆነ ይገመታል፡፡
የዳውሮ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ የአለባበስና አጋገጥ እንድሁም ባህላዊ ምግቦችና የአመጋገብ ሰርዓት ያለው ማህበረሰብ ክፍል ነው።ከባህላዊ ምግቦችም በጥቅቱ ስንመለከት ስልሱዋ፤ ቡራቱዋ፤ ኡታ፤ ሱልሱዋ፤ ታንጩዋ፤ አይብዛ፤ ተፔላ፤ ሱልአ፤ ባጭራ፤ ኩቡዋ፤ሀውዙዋ፤ ባሹማ፤ የመሳሰሉት ከብዙዎች ጥቅቶች ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት የዳውሮ ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች አብዛኛዎቹ የምሰሩት ወይንም የሚዘጋጁት ከዳውሮ ቅቤ ነው። ይህንን ስንገልጽ በጣዕሙ ልዩ የሆነው የዳውሮ ቅቤና ዳውሮ የማይለያዩት የማይነጣጠሉት ትልቅ ምስጥር አሏቸው። በአከባቢው በብዛት የቅቤና የማር ምርቶች ይገኙበታል።
በዞኑ በአብዘኛው ደጋማ አከባቢዎች ጥቅጥቅ ያለ ጫካ የምመስል የቀርከሃ ውጤቶች ይገኙበታል።
በማህበራዊ ዘርፍ ጤና ስንመለከት 182 ጤና ኬላ 21 ጤና ጣቢያ 3 ሆስፒታሎች፣ 440 ትምህርት ቤቶች ከዚህ 51 ሁለተኛ ደረጃ 389 አንደኛ ደረጃ ናቸው።
ዞኑ በርካታ ተፈጥሮአዊ፤ባህላዊና ታርካዊ ቅርሶችን የያዘ ሲሆን ከተፈጥሮአዊ ቅርሶች መካከል በዋናነት በዳውሮና ኮንታ ዞኖች መካከል የምገኘው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ አንዱና ዋነኛ ነው።
በባህላዊ ዘርፍ “ቶክ በአ” (የብሄሩ ዘመን መለወጫ) ወይም የአሮጌ ዓሜት መሰናበቻና የአድሱ ዓሜት መቀበያ በዓል ከባህላዊ ቅርሶች መካከል ዋነኛውና ቀዳምው ነው።
የዳውሮ ብሔር የራሱ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ቀመር ያለ ሲሆን የዘመኑ አቆጣጠር ልከቱ የጨረቃ ቅርጽ ይዘት መውጫና መጥለቅያ ሰዓትን ተከትለው የተቀመረ ነው።
በዞኑ ውስጥ ተፈጥሮአዊና ባህላዊ ቅርሶች ብቻ ሳይሆን ታርካዊ ቅርሶችም ይገኙበታል። ከታርካዊ ቅርሶች መካከል በ16ኛው ክፍለ ዘመን ተጀምረው በ18ኛው ክፍለ ዘመን እንደተጠናቀቀ የሚነገረው የዳውሮ ደረቅ የድንጋይ ካብ ሀላላ ኬላ፣ የኮይሻ የነገስታት መናገሻ ካቲ ጋጿዋ ፤ በቶጫ ወረዳ የሚገኘው የአንጋላቲ ጋቤ የፍርድ ዙፋን /ችሎት/፣ በአለለም ረጅሙ የትንፋሽ ሙዝቃ መሣሪያ ዲንኬና ባለ ጣዕመ ዘማው ህጽጼ፣ የጥንት ዳውሮ ብሔር አኗኗር የነገስታት ሁኔታ በስዕል መልክ የያዘው ባህላዊ የዕደ ጥበብ ምረት ‘ማንቻላ’ በዋናነት ይጠቀሳሉ።
ከቱሪስት መዳረሻ አንፃር፦ ሀላላ ኬላ በዳውሮ ንጉሥ ሀላላ ስም የተሰየመው ሀላላ ኬላ ሪዞርት ውብ ባህልና ድንቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለው ዞን ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡ ንጉስ ሀላላ ዳውሮን ከመሩ 14 ነገስታት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ የሀላላ ኬላ ሪዞርት በተሰራበት ስፍራ በትውልዶች ቅብብሎሽና ዳውሮን በመሩ ነገስታት አስተባባሪነት ጠላትን ለመካላከል እንዲያስችል የካቲ ሀላላ የድንጋይ የድንጋይ ካብ/ኬላ ተሰርተዋል፡፡
“ካቲ ሃላላ ኬላ” በሰባት ረድፍ የተደረደሩ የድንጋይ ካቦችና ሰባት በሮች አሉዋቸው፡፡ የድንጋይ ካቡ ሰባት ረድፎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው 175 ኪ.ሜትር ርዝመት አላቸው፡፡ በድምሩ 1225 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡
በዳውሮ ዞን ብዙ ክስተቶችን ያስተናገደው ይህ ታሪካዊ ስፍራው ወደ ቱሪስት መዳረሻነት ለመቀየር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አፍላቅነት የካቲት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ነው የግንባታ ስራው የተጀመረው፡፡ ሪዞርቱ 12 ሄክታር ላይ ያረፈ ሆኖ ቪላዎቹ የአካባቢውን ማህበረሰብ ባህላዊና ዘመናዊ የቤት አሰራር ጥበብ ተከትለው የእግረኛ፣ የሳይክልና የመኪና መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት ነው።
የሀላላ ኬላ ሪዞርት 3 ዓይነት ቪላዎችን ይዞ በተናጠል ለሚመጡ እንግዶች 10 ቪላዎች፣ 8 ደግሞ በቤተሰብ ደረጃ ለሚመጡ ባለሁለት መኝታ ያላቸው እንዲሁም ሁለቱ ቪላዎች ፕሬዝደንሻል ደረጃ ያላቸው ቅንጡ ማረፊዎች ናቸው፡፡
]
255 ሰዎችን መያዝ የሚችል የስብሰባ አዳራሽ፣ ሬስቶራንት፣ ማሳጅና ስፓ፣ ጂም፣ የመኪና ማቆሚያ፣ የዳውሮዎችን ባህላዊ ቅርሶችና ባህላዊ ልብስ መሸጫ የያዘ ሙዚዬም አካቶ ይዟል።
የሀላላ ኬላ የቱሪስት መዳረሻ ሪዞርት የነበረን ገጸ በረከት በማልማት ለቱሪስት መዳረሻነት እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥቅም እድል የፈጠረ ፕሮጀክት ነው፡፡
ሌላይኛው የቱሪስት መዳረሻ በዞኑ ውስጥ
በርካታ ዋሻዎችና ፏል ውሃውች ያሉት ስሆን ካቲ ሁሉቆ ዋሻ፣ ሻሊ ዋሻ፣ አድኖ ዛላ ዋሻ፣ ያኮ መንቲያ ዋሻዎች፣ ማሎ ዋሻ፤ ፍል ውሃዎች መካከል ደግሞ ሽቃ ፍል ውኃ፣ የዳራ ፍል ውኃ፣ የሶግዳ ፍል ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
