ፋይዳ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ እያንዳንዱ ህብረተሰብ መታወቂያውን በመያዝ መገልገል አለበት: አቶ በላይ ተሰማ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ (ፋይዳ) ማጠናከሪያ መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።

በማጠናከሪያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ ፓርቲው በለውጡ ካመጣቸው በርካታ ስትራቴጂዎች አንዱ ፋይዳ መታወቂያ ነው ብለው ይኸውም አንድ ሰው ራሱ ብቻ መሆኑን የሚያመለክት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ በላይ አክለው ይህ ንቅናቄ በክልሉ ባሉት ብዝሃ ዋና ከተሞችና ዞኖች ድረስ የሚካሄድ በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት ለማግኘት ወሳኝ የሆነውን መታወቂያ ካርድ እንዲይዙ አሳስበዋል።

በመድረኩ የክልሉ እና የዞን አመራርና ባለሙያ፣ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ገለፃውን ተከትለው ከኢትዮ ተሌኮም ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ቦታ ላይ የተገኙ ባለሙያዎች ለመታወቂያው እየተመዘገቡም ነወ።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *