




ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማዕከል ያደረገ የብሔራዊነት ትርክት ለማጽናት ወጣቶች የመሪት ሚናቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባቸው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ተናገሩ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ለወጣቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ በዛሬው ዕለት መስጠት ጀምሯል።
በስልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገራችን የነበረውን ምስቅልቅል የሆነውን የፖለቲካ ፣የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ስብራቶችን በተጨባጭ በመቀየር ባለፉት ዓመታት በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
ብልጽግና ፓርቲ ለወጣቱ ትልቅ ትኩረት የሚሰጥና ወጣቱን የሚያቅፍ ብቻ ሳይሆን በፓርቲ አደረጃጀት የወጣቱን አደረጃጀት በመፍጠር ድጋፍና ስልጠና በመስጠት ሀገራችን እንደ ሀገር እንድትቆምና ህዝባችን እንደ ህዝብ እንዲቆም እየሰራ ያለ ጠንካራ ፓርቲ ነው።
በፓርቲ ግንባታ ና ተቋም ግንባታ ላይ ትኩረት ስጥቶ ለወጣቱ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት አቶ ፍቅሬ ጠንካራ ፓርቲ እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
የልዩነትና ከፋፋይና ትርክቶችን በማረም ለህብረብሔራዊ አንድነታችን መሠረት የሚሆን የብሔራዊነት ትርክት ለማስረጽ ወጣቶች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ወጣቱ ከስራ ጠበቂነት መንፈስ በመላቀቅ ስራ ፈጣሪ በመሆን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነን ከማረጋገጥ ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት 7/24 በመስራት ድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ወጣቶች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ግንዛቤ አዳብረው በቀጣይ በተዋረድ ለሎች ለማጋራት ኃላፊነታቸውን መወጣት ይገባል ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን እንደገለጹት ሀገራችን ለወጠነችውን ብልጽግና ጉዞ የበኩላቸው እንዲወጡ አሳስበዋል።
ሀገር የሚገነባው በጋራ ትርክት መሆኑን የገለጹት አቶ ደግፌ አስተሳሳሪ ገዥ ትርክት ለሀገር ግንባታ ያለውን ፋይዳ በውል በመገንዘብ ወጣቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በፓርቲ ተቋማት ግንባታ ፣ብሔራዊነት ገዥ ትርክት፣ መሪነትና ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት መጀመሩን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
