



የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ-ኃይል በአምስት ዞኖች ላይ በኦዲት ያገኛቸዉን ግኝቶችና ተቋማት የሰጡት ምላሽ ላይ የግምገማና የማስተካከያ ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በቦንጋ ክላስተር ላይ ያሉ የክልል ተቋማት፣ በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ወረዳዎችና የዞኑ ፋይናንስን የሚመለከት የኦዲት ግኝት መሆኑም ተመላክቷል።
የክልል ግብርና ቢሮ፣የቦንጋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ፣የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ፣ገብረ ጻዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣የገዋታ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት፣የጨና ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤትና የዴቻ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚና ልማት ጽ/ቤት የኦዲት ሪፖርታቸውን አቅርቧል።
የኦዲት ግኝት አፈፃፀማቸውን መሰረት በማድረግ አጠቃላይ የክልሉ ኦዲት ግኝት ግበረ-ሀይል ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተመላክቷል።
የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ እና የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በቦንጋ ክላስተር ላይ ያለዉን ግምገማ መድረክ እየመሩት ነው።
መረጃዉ የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።
