የጠቅላይ ሚኒስትር ኢንሸቲቮች ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙ ተገለጸ

Spread the love

ለአንድ አገረ መንግሥት ግንባታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቀናጅተው መሥራት ወሳኝ መሆኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ገለጹ

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት የንጉሥ ሃላላ ሎጅና ሌሎች ታሪካዊ ቦታዎችንና ቅርሶችን ለመጎብኘት ወደ ዳዉሮ ዞን ገብተዋል።

የንጉሥ ሃላላ የድንጋይ ካቦችን፣ የጊቤ III ሃይድሮ ኤሌክትሪክ የኃይል ማመንጫ የሰው ሰራሽ ሐይቅና በጠቅላይ ሚኒስትር ሃሳብ አመንጪነት የተገነባው የሃላላ ሎጅና ሙዚየም እየጎበኙም ይገኛሉ።

በጉብኝቱ ወቅት የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የዲሞክራሲያዊ ባህል ግንባታና የምርጫ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አሸብር ታደሠ እንደገለፁት በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ወሳኝ በመሆኑ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንዲቻል የጋራ መድረኮች ተዘጋጅተው ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

ከእነዚህ መድረኮች መነሻ የብልጽግና ፓርቲ እንደአገር መንግሥትን መምራት ከጀመረ ወዲህ በርካታ የልማት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ኢንሼቲቭም ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ገልጸዋል።

በጉብኝታቸውም የሃላላ ኬላን የተመለከቱት ሲሆን የግንባታ ሂደት በሦስት መንግሥታት ዘመን በትውውልድ ቅብብሎሽ የተጠናቀቀ መሆኑ በቀጣይ ለሀገር ግንባታ የሚሆኑ ግዙፉ ፕሮጀክቶች ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ማሣያ መሆኑንም አስረድተዋል።

በአገር ደረጃ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰባት አካባቢዎች ላይ እንዲጎበኙ የተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ

በበኩላቸው ሰሞኑን በሀገር ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዓቢይ አሕመድ (ዶክተር) ጋር ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ስለአገር ሰላማዊና ቀጣይ ዕድገት እየተወያዩ እንደሚገኙ ይታወቃል።

ይህንን ውይይት ተከትሎ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችንና ታሪካዊ የቱሪስት መደረሻዎችን እንዲጎበኙ ዕድል ተመቻችቷል ።

በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሳብ አመንጪነት የለማው ታሪካዊ የንጉሥ ሃላላ ሎጅ አካባቢውን ከማስተዋወቅ ባሻገር የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም አቶ ዳዊት ተናግረዋል።

ወደ ዳዉሮ ዞንም በዛሬው ዕለት ያቀኑ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የሀላላ ሎጅና በአካባቢው ያሉ ታሪካዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ተደርጓል።

ከጉብኝቱ መልስ ለጣቢያችን አስተያየት ከሰጡት መካከል የአፋር ነፃ አውጪ ግንባር ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ ሃጂ እስማኤል መሐመድ አብደላ እንደሚሉት የአገር አንዱ አካል የሆነው አካባቢ ሳያውቀው መቆየታቸው ቁጭት ፈጥሮባቸዋል።

አሁን ላይ ግን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ታሪካዊ ቅርሶች በጠቅላይ ሚኒስቴር ሃሳብ አመንጪነት ተገንብተውና ለምተው የሚገኙት እንዲጎበኙ መደረጉ ደስታን እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።

የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄና የጋራ ምክር ቤት የፌዴራል ወጣቶች ክንፍ ምከትል ሰብሳቢ አቶ ጥጋቡ ደጄኔ በበኩላቸው ለአገር ኢኮኖሚ የድርሻውን እየተወጣና ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል እየፈጠረ የሚገኙ የጠቅላይ ሚኒስትር ኢንሸቲቭ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ከመስማት ይልቅ በዓይን መመልከታቸው የተሻለ ዕውቅናን ለመስጠት ያስችላልም ብለዋል።

በቀጣይም አንድ ጠንካራ አገረ መንግሥት ለመገንባት እንዲቻል የፖለቲካ የጋራ ምክር ቤቶች ተቀናጅተው መሥራት አበርክቶቱ ላቅ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል ሲል ደሬቴድ ዋካ ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *