የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ተወያዩ፡፡

Spread the love

የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር አድርገዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች እውነትና ዕውቅት ብቻ የሚፈልቅባቸው ተቋማት ናቸው::

ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማርና የምርምር ማዕከል መሆናቸውን ያነሱት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ዩኒቨርሲቲዎች መንግስት በዘርፉ ያስቀመጣቸውን ዓላማና ግብ መሰረት በማድረግ መስራት አለባቸው ብለዋል::

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደገላ ኤርገኖ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው አካላት ጋር በተደረገው ዉይይት ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ግብ ተጥሎ ተግባር ተኮር ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል::

ተቋሙ የጀመራቸው መልካም ስራዎችን ማስቀጠል እና የሚሻሻሉ ተግባራትንም ለይቶ የማሻሻል ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል::

የዩኒቨርሲቲው የ2017 በጀት ዓመት የድጋፍና ክትትል ግብር መልስ እየቀረበ ሲሆን በዉይይቱ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል::

በውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የስራ ሀላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የካፋ ቴሌቪዥን ድርጅት ነው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *