




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ሁለተኛው ዙር ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የኢፌደሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ በጋራ በመሆን አስጀምረዋል።
የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ”ከጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ጎን ጎን በቦንጋ ከተማ ቢሻው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጊቢ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አከናውነዋል።
በትምህርተት ቤቱ ጊቢ ውስጥ የተተከሉ የአረንጓዴ አሻራ ችግኞች የተለያዩ ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆኑ እንደሀገር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚኖረው ሚና ጉልህ ነዉ።
በመረሐ ግብሩ የፌደራል፣የክልል፣የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የከተማው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በፍቅር ከበደ
