




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ በጋራ በመሆን ነው ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ባደረጉት ንግግር የአካባቢያችን ለዜጎች ምቹና አረንጓዴ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የራሳችንን ጤና ልማት የሚናመርትበት ስለሆነ በተከታታይ የሚናከናነው ሀገራዊ ኘሮግራም ነው ብለዋል።
የቆሻሻ ብቻ ሳይሆን የአየር ብክለትንም የሚንከላከልበት በመሆኑ በከተማም ሆነ በገጠር ከአረንጓዴ ልማት ስራ ጋር አስተሳስረን የሚንቀጥል ይሆናል ብለዋል።
“ጹዱ ኢትዮጵያ” አካባቢን ከብክለት ነፃ በማድረግ ለነዋሪዎች ምቹ ውብ እና ጹዱ አከባቢን ለመፍጠር ያለመ በመሆኑ መላው የከተማችን ህብረተሰብ ይህንን ተገንዝቦ በዘመቻ እንዲሳተፉ መልዕክታቸውን አስተልፏል።
እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ደጅ እና አካባቢ ማጽዳት ከቻለ ከተማው ጽዱ እንደሚሆን በመገንዘብ ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የአከባቢው ጽዳት ከቀድሞ የበለጠ መጠበቅ እንዳለባቸው ጥሪ ቀርቧል።
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በወቅቱ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው ጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ የሁል ጊዜ ባህል በማድረግ አጠናክረን ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
ጽዱ ኢትዮጵያን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ራስን መቻል ያስፈልጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ንቅናቄው በከተማም ሆነ በገጠሩ አከባቢ የተጀመሩ ኮሪደር ልማት ጋር በማስተሳሰር አከባቢያችን ውብና አረንጓዴ የማድረግ ሥራዉ ይጠናከራልም ብለዋል።
የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ ባስተላለፋት መልዕክት ንቅናቄውን ስናስጀምር የአባቶቻችንን ምሳሌ በማድረግ አካባቢውንና መጠበቅና መንከባከብ አለብን ብለዋል።
ጽዱ አካባቢን እንዲሁም ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም ዜጋ የአከባቢውን ፅዳትና ውቤት የማስጠበቅ ስራን ባህል አድርጎ መስራት እንዳለበትም ተጠቁመዋል።
የክልል፣የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ አመራሮች፤ የከተማው አስተባባሪ አካላት፤ የከተማው ህብረተሰብ ተሳትፈዋል ።
በካሳሁን አሰፋ
