የዳውሮ ዞን ምክር ቤት አቶ ዳዊት ገበየሁን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ።

Spread the love

የዳውሮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ሥራ ዘመን 11ኛ አስችኳይ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ጉባዔ አቶ ዳዊት ገበየሁ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንዲሆን የቀረበውን ፕሮፖዛል ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል ።የዳውሮ ዞን ምክር ቤት በአስቸኳይ ጉባኤው በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የቀረበውን የሹመት ፕርፓዛል ተቀብሎ አጸደቀ።

በተጨማሪም አቶ አስፋው ደሳለኝን የዳውሮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ እንዲሆኑ የቀረበውን ፕሮፖዛል ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

ሹመታቸው የፀደቀላቸው ኃላፊዎችም በምክር ቤት አባላት ፊት ቀርበው ቃሌ መሃላ ፈጽመዋል ሲል የዳውሮ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *