በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተደረገው የባህር በር ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ወጣቱ ትውልድ በጋራ እንዲቆም ጥሪ ቀረበ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ሰብሳቢ ወጣት ይስሃቅ ንጉሴ እንደተናገረው ሀገራችን በታሪክ ወደብ የነበራትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደብ አልባ ሆና መቆየቷን አስታውሰዋል ፡፡

ሀገራችን የወደብ በር ማግኘቷ የገቢና ወጪ ንግድ ስርዓትን ከማሳለጥ ባሻገር የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ወጣት ይስሃቅ ተናግሯል ።

በቀጠናው እየተስተዋለ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ የተረጋጋ ከማድረጉም በላይ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲዳብር ያግዛል በማለት ተናግሯል ፡፡

የሀገራችን ወጣቶች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነና ከአቅም በታች በመስራት በኢኮኖሚው ውጤታማ እንዳልሆኑ ወጣት ይስሃቅ ተናግሯል ።

የባህር በር ባለቤት ሲኮን ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አዳዲስ የኢኮኖሚ ፓኬጆችና ፕሮግራሞች ስለሚነደፉ ለሀገራችን ወጣቶች ትልቅ ተስፋን ይዞ የመጣ ስምምነት ነው እንደሆነም ገልጿል።

የሀገራችንን ልማትና ዕድገት የማይፈልጉ አካላት ሰለባ ከመሆን ራሳችንን በማራቅ ሀገራችን የያዘችውን የልማት ጉዞ እውን ለማድረግ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ለተቀረው ዓለም ግንዛቤ በመፍጠር ለብሔራዊ ጥቅማችን መሳካት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል በማለት ወጣት ይስሃቅ መልዕክቱን አስተላልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *