ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተከበረው ምክር ቤት ካነሷቸው ነጥቦች፦

Spread the love

➡️ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋልታ ነው በርካታ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሳተፍበት ሴክተር ነው፤ በአንድ ዘርፍ ላይ ጥገኛ የሆነ ኢኮኖሚ ስለማያዋጣ ብዝኃ ዘርፍ እና ብዝኃ ተዋናይ በማድረግ ብዙ ጥቅም ለማግኘት ነው በግልፅ መንገድ ሪፎርም የጀመርነው፡፡

➡️ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አለባት፤ አምርታ መብላት የማትችል ሀገር ብሔራዊ ጥቋሟን ለማስጠበቅ ትቸገራለች፡፡

➡️ባለፉት ጥቂት ዓመታት በኢትዮጵያ 27 ሚሊየን ገደማ ሰዎች በሴፍቲኔት የታቀፉ ተረጂዎች ነበሩ፤ ኢትዮጵያ መለመን የለባትም ልጆቿ ተግተው፤ ሰርተው ከልመና ራሳቸውን መገላገል አለባቸው የሚለው ዕምነት ፍሬ አፍርቷል፡፡

➡️ዘንድሮ 23 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት መውጣት ችለዋል፤ ኢትዮጵያ ሙሉ በመሉ ከሴፍቲኔት እና ከተረጂነት የተላቀቀች ሀገር እንድትሆን ከሁላችንም ብዙ ስራዎች ይጠበቃሉ፡፡

➡️23 ሚሊየን የሴፍትኔት ተረጂዎችን ማላቀቅ ተችሏል፣ ቀሪ 4 ሚሊየን በላይ ተረጂዎችን ከእርዳታ ለማላቀቅ እና ወደ አምራችነት ለማሸጋገር በትኩረት ይሰራል፡፡

➡️ባለፈው ዓመት 26 ሚሊየን ሄክታር መሬት ታርሶ ነበር፤ በዚህኛው ዓመት ደግሞ 31 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ተችሏል፤ ኢትዮጵያ ባፈው ዓመት በሁሉም ዓይነት የሰብል ምርቶች 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ኩንታል ምርት ነው የሰበሰበችው፣ ዘንድሮ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል መሰብሰብ ተችሏል፡፡

➡️በዚህ ዓመት እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ ስድስት ከፍተኛ ግድቦች ይመረቃሉ፡፡

➡️በዓመት ሁለት እና ሶስት ጊዜ የማምረት ልምምዳችን የጨመረ ሲሆን፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ብለን የጀመርነው ሥራ በርካት ለውጦችን ማምጣት ችሏል፡፡

➡️የሌማት ትሩፋት ብለን በጀመርነው ሥራ የወተት እና የእንቁላል ምርቶችን ማሳደግ ችለናል፡፡

➡️ምርታማነት እያደገ ሲሆን ከውጭ የምናስገባቸውን ምርቶች መተካት ችለናል ይህንን አጠናክረን ከቀጠለን በብዙ ዘርፍ ውጤታም ልንሆን እንችላለን፡፡

➡️የግብርናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ያገኘ እና ትልቅ ውጤት ያመጣ ነው፤ ለአጠቃላይ ዕድገታችን ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *