
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
በእኛ በኩል በትግራይ ምድር አንድም ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የለንም ከቻልን የማልማት ፍላጎት ነው ያለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በትግራይ ክልል ቴሌኮም፣ ባንክ፣ መብራትና ፋብሪካዎች ስራ መጀመራቸውን እና መንግስት መቋቋሙን አስታውቀዋል፡፡
ተፈናቃይን በሚመለከት ራያ 100 በመቶ መመለሳቸውን ገልጸው፤ ምን ቀረ ካላችሁ ወልቃይት ያሉ ተፈናቃዮች አልተመለሱም እነዚህንም ለመመለስ ነው እየተሰራ ብለዋል፡፡
ትግራይ ሳትቀየር ኢትዮጵያ ትቀየራለች የሚል እምነት ስለሌለን የፌደራል መንግስት ትግራይ ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ 100 በመቶ ጦርነት እንደማይፈልግ ገልጸው፤ ትግራይ የሚያስፈልገው ሰላም እና ችግሮችን በውይይት መፍታት መሆኑን ይገባል ነው ያሉት፡፡
የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትግራይ ዳግም ወደግጭት እንዳይገቡ መስራት አለባችሁ ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
