የማህበረሰቡን የሰላም ሚና በተመለከተ

Spread the love

“ማህበሰቡ ሳይሸሽግ የታጠቁ አካላትን አትግደሉ፣ አትግደሉልኝ፣ እናንተም አትሙቱልኝ ማለት አለበት።

ልጆቼን ፈተና እንዳይፈተኑ እንዳይማሩ አትከልክሉ፣ እንዳንሰራ አታድርጉ፣ ማዳበሪያ እንዳይመጣ አታድርጉ ማለት አለበት። ይህንን ሰሞኑን የአማራ ህዝብ በቅርቡ አሳይቷል፤ ሰላም ልማት እፈልጋለሁ ብሏል፤ በቃኝ ብሏል። ይህ ለሁሉም ግልፅ መልዕክት ነው። ለዚህ የህዝብ ጥያቄ የከበረ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል። ማንኛውም ሰው ወደ ስልጣን ሲመጣ ከዚህ ቀደም ምን ሰርተህ ታውቃለህ፣ ግብር ከፍለሃል ወይ፣ ማንን አገለገልክ፣ ታማኝ ነህ ወይ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ህዝቡ ይህን እየጠየቀ ማጥራት አለበት። ማህበረሰቡ የሰላምና የብልሹ አሰራር ችግርን በዘለቂነት ለመፍታት ሚናውን መወጣት አለበት። ሰላም ሁልጊዜ የሚገነባ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ግጭቶች ተፈትተው አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል። አንጻራዊ ሰላም ባይኖር ግብርናው፣ ማዕድኑ፣ ቱሪዝሙ አያድግም ነበር። አሁንም ቀሪ ችግሮችን በመፍታትና በጋራ በመስራት የሰላምን ዘላቂነት ማረጋገጥ ይገባል።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *