







የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡
በዚህም መሠረት፦
1ኛ.የ39ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔን መርምሮ አፅድቋል።
2ኛ.በመቀጠልም የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል።በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን 22 የግብርና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለመሰማራትከ 500 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ የቀረቡ ኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።
3ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በተለያዩ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቷል። በዚህም
ሀ.የሥነ-ህዝብ ምክርቤትን ለማቋቋም ፣ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ደንብ ላይ ተወያይቶ ወደ ስራ እንዲገበ ወስኗል።
ለ.የመንገዶች ባለስልጣን ሥልጣንና ተግባር ለመደንገግ የወጣ ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
