በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብልጽግና እሳቤዎች ቅኝት በርካታ ተግባራት በስኬት ተከናውነዋል ፦አቶ በላይ ኮጁአብ

Spread the love

‎በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብልጽግና እሳቤዎች ቅኝት በርካታ ተግባራት በስኬት ማከናወን እንደተቻለ የቦንጋ ብዝሃ ማዕከል የኢኮኖሚ ዘርፍ ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ በላይ ኮጁአብ ገለጹ

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ የቦንጋ ብዝኃ ማዕከል የኢኮኖሚ ዘርፍ ብልጽግና ህብረት የ2017ዓ.ም የአባላት ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

‎የቦንጋ ብዝሃ ማዕከል የኢኮኖሚ ዘርፍ ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ በላይ ኮጁአብ በማጠቃለያ ኮንፈረንሱ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህብረቱን ተቋማዊ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ፈርጀ ብዙ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

‎አመራሩና አባሉ በተሰማራበት መስክ ሁሉ አገልጋይ ተኮር እሳቤን በመላበስ ለብልጽግና ጉዞ ስኬት መሰረት የሚጥል ውጤት ተመዝግበዋል።

‎በፓርቲው አደረጃጀትና አሰራር መሠረት የብልጽግና ቤተሰብና ህብረት ተልዕኮውን በብቃት መፈጸም እንዲችሉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት አቶ በላይ የአባሉቱ የፖለቲካ አስተሳሰብ ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ አየተጠናከረ መምጣቱን ገልጰዋል።

‎በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት አቶ አለማየሁ አይበራ ፓርቲያችን ብልጽግና በመደመር መንገድ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል ተብለዋል።

‎ፓርቲያችን ያነገባቸውን ህልሞችን ወደ ሚጨበጥ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

‎የፓርቲና የመንግስት ኢኒሼቲቦች በበጋ ስንዴ ልማት፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በሌማት ትሩፋት ፣በቡና ልማት፣ በሰው ተኮር አሳቤዎች እንዲሁም በሌሎች መስኮች አበረታች ውጤቶች ሊመዘገብ የቻለው አመራሩን፣ አባሉንና የፓርቲው እሳቤዎችን በላቀ ብቃት መተግበር መቻላቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

‎አመራሩና አባሉ እስካሁን የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በልዩ ቁርጠኝነት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

‎ልማትን የሚያደናቅፉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን አባሉ አምሮ መታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎የ2017 ዓም የብልጽግና የህብረት አፈጻጸምና የ2018 ዓም ዕቅድ ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል ሲል የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *