


በጉባኤው ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸም ማቅረብ ጀምረዋል ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፡-
በበጀት ዓመቱ በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ጸጋዎችንና የልማት ኃይሎችን በመጠቀም ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ሁለንተናዊ እድገት ማስመዝገብ የሚያስችሉ ክልላዊ ስራዎች ተከናወነዋል ፡፡
በአብዛኛው ዘርፎች ካለፉት ዓመታት የተሻለ ውጤት ማስመዘገብ ተችሏል፡፡
2680 አመራሮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የአመራር ብልሽት ውስጥ የገቡ 150 አመራሮች ከኃላፊነት እንዲነሱ ተደርጓል፡፡
ክልላዊና አካባቢያዊ አቅምን መሠረተ ያደረጉ የተለያዩ የግብርና ኢንሸቲቮችን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ መስኮችን ማስፋት ተችሏል።
የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ከተረጂነት መላቀቅና የኑሮ ውድነትን መቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን እየተከናወኑ ነው፡፡
ዘላቂ ክልላዊ ሠላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት የተሻለ ሠላማዊ አከባቢ መፍጠር ተችሏል፡፡
በመኤን ብሔረሰብና በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ማህበረሰብ ውስጥ ከግማሽ ምዕተ ዓመታት በላይ የዘለቀውን በደልና ቁርሾ የሀገር ሽማግሌዎችን በማሳተፍ በእርቅና ይቅርታ መቋጨት ተችሏል፡፡
በክልል መደበኛ ካፒታል፣ በተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ 87 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በ601 ሚሊዮን ብር ወጪ ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡
ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በቦንጋ ከተማ ባለ ሁለት ወለል የመደመር ትውልድ ቤተ መጽሐፍት ዘመናዊ ህንጻ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ፣
በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የበጀት ድጋፍ በሱሪ ወረዳ የቱልጊት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ተጠናቆ ለ2018 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ሆኗል፡፡
ቀልጣፋና የዘመነ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የክልል ቢሮ ህንጻ በአራት የክልሉ ብዝሃ ከተሞች በ 5.7 ቢሊዮን ብር እንዲጀመር ተደርጓል፡፡
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ኢንሼቲቪ ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸው
ለሚዛን አማን አዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለልማት ተነሺዎች የካሣ ክፍያ የሚውል 20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በክልሉ መደረጉ
የቴፒ ቀላል አይሮፕላን ማረፊያ በረራውን በይፋ እንዲጀምር ተደርጓል፡፡
የከተማ እና የገጠር ኮርደር ልማት ሥራዎችን በቁርጠኝነት በመምራት አበረታች ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡
በበጀት ዓመቱ 881 የአረጋዊያን እና የአቅመ ደካሞችን ቤት አዲስ ግንባታ እና ጥገና ሥራ መሥራት ተችሏል፡፡
41 የገጠር እና የከተማ ወረዳዎች የቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ተጠናቋል ፡፡
በበጀት ዓመቱ 421 ሺህ 541 ቤተሰብ አባላትን በማዐጤመ አገልግሎት ሥር እንዲታቀፉ በማድረግ 445.7 ሚሊዮን ብር ከከፋይ አባላትና ከተናጠል ድጎማ በመሰብሰብ የማዐጤመ ሽፋንን ወደ 75.6% ማድረስ ተችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ 1.06 ቢሊዮን ብር የጥሬ ገንዘብ ብድር፣ የግብዓት ዕዳ እና የማህበራዊ ዋስትና ዕዳ ተመልሷል፡፡
በበጀት ዓመቱ ምንም ዓይነት ተጨማሪ ብድር ውስጥ ሳይገባ የመንግሥት ሰብአዊ ወጪዎችንና የልማት ተግባራትን በራሳችን አቅም መሸፈን ተችሏል፡፡
በታጠቅ አበበ
