ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለክልሉ ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ማቅረባቸውን ቀጥለዋል ፡፡

Spread the love

ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት ሪፖርት በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች ው ጤታማ መሆናቸውን አብራርርዋል ፡፡በዚህም ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፡-

👉በዋና ዋና የአዝርዕት ሰብሎች በመኸር፣ በበጋ መስኖ እና በበልግ ወቅት 745,090.5 ሄ/ር ማሳ በዘር ተሸፍኗል፡፡

👉በበጀት ዓመቱ 20 ሚሊየን 632 ሺህ 359 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል፡፡

👉በበጋ መስኖ ስንዴ 5,017 ሄ/ር መሬት በዘር በመሸፈን 149 ሺህ106 ኩንታል ምርት ተገኝቷል፡፡

👉የኩታ ገጠም እርሻን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ 167 ሺህ 426 ሄክታር መፈጸም ተችሏል፡፡

👉በሆርቲካልቸር ሰብሎች በአትክልት፣ሥራሥር፣ እንሰትና ፍራፍሬ በበልግ መስኖና መኸር አዝመራ 326 ሺህ 698 ሄክታር ለምቷል ፡፡

👉ከምርት አንጻርም 66 ሚሊን 958 ሺህ 777 ኩንታል ምርት ተገኝቷል።

👉የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት አኳያ 132,000 ኩንታል ታቅዶ 156,085 ኩንታል ማቅረብ ተችሏል ፡፡

👉የምርጥ ዘር አቅርቦትን በተመለከተም 80 ሺህ 064 ኩንታል ለማቅረብ ታቅዶ 82 ሺህ 507 ኩንታል ቀርቦ ተሰራጭቷል፡፡

👉በአረንጓዴ አሻራ ተግባር አፈጻጸም በግብርና መዋቅር ብቻ በክረምት የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው 145,628,040 ችግኞች በመትከል 44‚553 ሄክታር መሬት ተሸፍኗል፡፡

👉የሌማት ትሩፋትን ውጤታማ ለማድረግ አኳያ በወተት 186 ፤በዶሮ 148 ፤ በንብ 327 ፤በዓሳ 14 እንዲሁም በቀይ ስጋ 167 መንደሮችን በማደራጀት እየተሰራ ነው ፡፡

👉የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል እንስሳት ዝርያን ለማሻሻል 56,726 ላሞችንና ጊደሮችን ማዳቀል ተችሏል።

👉በሁሉም እርባታ ደረጃዎች 357 ሚሊዮን ሊትር ወተት ማምረት ተችሏል።

👉የቡና ማሳ ሽፋንን ከማሳደግ አንጻር በበጀት ዓመቱ 88,546,348 የቡና ችግኝ በማዘጋጀት 87,944,188 ቡና ተተክሏል፡፡

👉ከቅመማ ቅመምና ሻይ ልማት ሥራዎች አፈፃፀም አንጻር ከነባር ለምርት ከደረሰ 75,064 ሄ/ር ማሳ ላይ 385,465.4 ቶን ምርት ተሰብስቧል፡፡

👉በበጀት ዓመቱ በቡና የታጠበና ያልታጠበ 48 ሺህ 153 ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል፡፡

👉የተለያዩ ችግኞችን በመትከል ክልላዊ የደን ሽፋን ከነበረበት ከ42.9% ወደ 43.8% ማድረስ ተችሏል፡፡

👉የነዳጅ ግብይት ስርዓት በኤሌክትሮኒክስ ግብይት አገልግሎት በሚሰጡ 33 የነዳጅ ማደያዎች 57,212,202 ሊትር ናፍጣ እና 9,208,740 ሊትር ቤንዚን ቀርቦ ተሰራጭቷል፡፡

👉በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 252 የንግድ ድርጅቶች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ።

👉በህገ-ወጥና በኮንትሮባንድ የንግድ እንቅስቃሴ 48,405,538 ብር የሚገመት ምርት ተይዞ ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

👉ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በግብርና 67 ፤ በኢንድስትሪ 25 እና በአገልግሎት ዘርፍ 22 አዲስ ፍቃድ መስጠት ተችሏል፡፡

👉በበጀት ዓመቱ 89 አነስተኛና መካከለኛ አዳዲስ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

👉ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር በቋሚ እና በጊዜያዊ 140,894 ዜጎች የስራ ዕድል በበጀት ዓመቱ የስራ ዕድል ተፈጥሯል ፡፡

👉በበጀት ዓመቱ ጠቅላላ ገቢ ብር 10 ነጥብ 07 ቢሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 9 ነጥብ 66 ቢሊየን (96%) መሰብሰብ ተችሏል፡፡

👉የክልላዊ ሀብት ግመታ ጥናት ማስጀመሪያ ምዕራፍ ስራዎችን ተጠናቀዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *