በማንኛውም የንግድ እቃ እና አገልግሎት ግብይት ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው ይታቀቡ_ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር



የንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ከሚደረገው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ ከደመወዝ ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በማንኛውም የንግድ እቃ እና አገልግሎት ግብይት ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ወይም ሰው ሰራሽ እጥረት ለመፍጠር ምርት የሚሰውሩ እና አላግባብ የሚያከማቹ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ እናሳስባለን ብለዋል።
መንግስት የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያ ለማድረግ ያስተላለፈው ውሳኔ የሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያግዝ በጎ ተግባርና አዎንታዊ እርምጃ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
የደሞዝ ማሻሻያው ከሀገራችን ጠቅላላ ህዝብ ቁጥር ከ2% የማይበልጠውን የመንግስት ሠራተኛ የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል መንግስት ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ የተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከዚህ በፊት ካለው ልምድ ለመገንዘብ እንደሚቻለው አብዛኛው የንግዱ ማህበረሰብ ሕግና ስርዓትን ጠብቆ የሚሠራ መሆኑ የሚያስመሰግን ቢሆንም የተወሰኑ በአፍቅሮተ-ነዋይ የታወሩ ነጋዴዎች ለሠራተኛው ኑሮ ማሻሻያ የሚደረገውን የደሞዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት መሯሯጥ ተስተውለዋል።
እንደዚህ አይነት ኢ-ሞራላዊ ያልተገባ ጥቅም ማግኛ ሩጫ ከንግድ ሥነ-ምግባርና ሞራል አኳያ ሲታይ አሳፋሪ ተግባር መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በአዋጅ ቁጥር 980/2008 እና 813 /2006 እንዲሁም በወንጀል ሕግ 1996 ተላልፎ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በማድረግ በማንኛውም የንግድ እቃ እና አገልግሎት ግብይት ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ወይም ሰው ሰራሽ እጥረት ለመፍጠር ምርት የሚሰውሩ እና አላግባብ የሚያከማቹ ሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን ብለዋል።
በተጨማሪም በየደረጃው የሚገኝ የንግድ መዋቅር ከሚመለከታቸው የፍትህ እና ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ የገበያ ማረጋጋት፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ በማጠናከር በአጥፊዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ እየተወሰደ የግብይት ሂደቱ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል እንዲደረግም አሳውቀዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
