የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገለጸ ።


በምክር ቤቱ የ2017 ዓመተ-ምህረት ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጀማል አባመጫ የምርጫውን መጠናቀቅ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ምርጫው በ502 የምርጫ ጣቢያዎች ከነሃሴ 9 እስከ 11 ቀን 2017 ዓመተ-ምህረት ሲካሄድ ቆይቶ በሰላም መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡
ኡለማዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችና የሙያ ማህበራት በየመስኪዶች በመገኘት መምረጥ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በምርጫ አፈፃጸም ዙሪያ ያጋጠሙ አንዳንድ ችግሮችን የመፍታት ሥራ መሠራትን ጠቁመው በሂደት ላይ የሚገኙ ጉዳዮች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡
ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ህዝበ ሙስሊሙን ጨምሮ ሁሉም የፀጥታ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ አቶ ጀማል ምስጋና ማቅረባቸዉን ቦንጋ ኤፍ.ኤም 97.4 ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
