በክልሉ 600 ሺህ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሳተፉ ነው።

Spread the love

በክልሉ 600 ሺህ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሳተፉ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 600 ሺህ ወጣቶች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ለፋና እንዳሉት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራው በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

አሁን ላይም 600 ሺህ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ እየተሳተፉ መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡

ወጣቶቹ በአረንጓዴ አሻራ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ እና መገንባትን ጨምሮ በአጠቃላይ በ14 ዘርፎች ነው የበጎ ፈቃድ ሥራ እያከናወኑ የሚገኙት፡፡

በአገልግሎቱ እስካሁን ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመው÷ በዚህም ከ380 ሚሊየን በላይ ብር የሚገመት ሥራ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

የክልሉ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ባህል እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *