የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሳ ምርታማነት በሶስት ዕጥፍ ማሳደግ አስችሏል – ግብርና ሚኒስቴር

Spread the love

የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሳ ምርታማነት በሶስት ዕጥፍ ማሳደግ አስችሏል – ግብርና ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የዓሳ ምርታማነት በሶስት ዕጥፍ እንዲያድግ ማስቻሉን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በጥቅምት 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ በይፋ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ግብ አልሟል።

በመርሃ ግብሩም የእንስሳትና ዓሳ ሃብት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት በማሳደግ ተጨባጭ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።

በግብርና ሚኒስቴር የዓሳ ሃብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ፋሲል ዳዊት(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ለዓሳ ሃብት ልማትና ምርታማነት ምቹ መደላልድል በመፍጠሩ የዓሳ ሃብት አጠቃላይ የምርት አቅም በሶስት እጥፍ አድጓል ብለዋል።

በቅርቡ ለምርቃት የሚበቃው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም በቀን እስከ 14ሺህ ኪሎ ግራም የዓሳ ምርት እያስገኘ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ሕዳሴ ግድብ ከሚያስገኛቸው የዓሳ ምርቶች መካከል ናይል ፐርች፣ ናይል ቴላፒ የተሰኙ እና የመሳሰሉት ከፍተኛ ዋጋና ምርት ሰጪ ዝርያዎች እንደሚገኙበት አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅትም የዓሳ ምርትን ከ255ሺህ ቶን በላይ በማሳደግ ለሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ስኬት የዓሳ ሃብት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዜጎችም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የዓሳ ሃብትን እንደጓሮ አትክልት ሁሉ በጓሮ የማምረት ደረጃ መሸጋገራቸውን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የዓሳ ሃብት ልማትና ምርታማነትም የተመዘገበው ስኬትም ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *