አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ስኬል ነው ተብሎ በየማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው መረጃ ውሸት ነው_ዶ/ር መኩሪያ ሀይል

የተፈቀደው አዲሱ የደመወዝ እስኬል ይህ ይመስላል የሚሉ ሃሰተኛ መረጃዎች በሶሻል ሚዲያ እየተለጠፉ ነው።
እነዚህን የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል በሚል በአንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚናፈሱ አሳሳች መረጃዎች ውሸት እንደሆኑና የሚለጥፉ ሰዎችም እንድተው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሚኒስትር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካይነት ብቻ የሚለቀቁ መረጃዎች በመንግስት የሚተገበሩ መረጃዎች መሆኑን መገንዘብ ጥሩ ነውም ብለዋል ሚኒስትሩ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
