ህዝብ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ማረም እንደሚገባ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር” በሚል መርህ ቃል ባለፉት ዐራት ቀና በቦንጋ ከተማ ስካሄድ የቆየው ክልል አቀፍ የአመራር ውይይት ተጠናቋል።






በመድረኩ ማጠቃለያ የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በየደረጃው ያለው አመራር ህዝብ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደርና የአግልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር መንግሥት በቁርጠኝነት እየሰራ መኾኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት።
በዚህም ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን ቀጣይነት ያለውን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በለውጡ መንግሥት የተጀመረው ተግባር እምርታዊ ለውጥ እያስመዘገበ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በቀጣይም ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የውጭ ተጋላጭነትን መከላከል እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ አብሮነትንና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚሸረሽሩ ተግባራት መከላከል ይገባል ብለዋል።
ኑሮ ውድነት ለመቋቋም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የገበያ ቁጥጥር ስርዓት ማሻሻል እንዲሁም የንግድ አሻጥር መከላከል ይገባል ያሉት ርዕሰመስተዳድሩ፤ በሁሉም ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን አቅም በፈቀደው መጠነ መፍታት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በየደረጃው የሚገኝ አመራር ህዝባዊነት ስሜትን የተላበሰ አገልግሎት በመስጠት የተጀማመሩ የኢኮኖሚ አርበኝነት በማጠናከር የገቢ አቅምን ለማሳደግ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ስልጠናው በአመራሩ ዘንድ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፈጠር የሪፎርም ሥራዎቻችንን ይበልጥ ውጤታ ለማድረግ የሚረዳ መኾኑን የጠቆሙት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን አመራሩ የማስፈፅምና የመፈፀም አቅሙን በማጎልበት የፓርቲው ራዕይ ለማሳካት ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች በበኩላቸው መድረኩ በሁሉም አመራር ዘንድ በሀገራዊ፣ በቀጠናዊ እና በአካባቢያዊ ነባራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ የፈጠር መሆኑን በመጠቀስ ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ እንደሆነም ተናግረዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
