ሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ መሰረቶች ናቸው – ኢንስቲትዩቱ
ሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ መሰረቶች ናቸው ሲሉ የፖሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ጸጋ ገለጹ።

ኢኒስቲትዩቱ “ሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች መደበኛ ባልሆነ ኢኮኖሚና በወጣቶች ላይ ያላቸው ሚና” በሚል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በዚሁ ወቅት የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፍቃዱ ጸጋ እንዳሉት፤ ሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች ጠንካራና የሚሊዮኖች መተዳደሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው።
እንዲሁም ለብዝኅ ኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት መዳበር እንዲሁም ለማህበራዊ እሴት ግንባታ መሰረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፎች የተደራጀና ቀጣይነት ያለው የፖሊሲ ድጋፍና ክትትል ክፍተት መኖሩን ጠቁመው፤ ኢንተርፕራይዞች ነጥረው እንዳይወጡ እንቅፋት እየፈጠረባቸው እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ኢንተርፕራይዞቹን ቀጣይነት ባለው መልኩ የኢኮኖሚ፣ የፈጠራና ክህሎት እንዲሁም የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ዋስትና መሆን የሚያስችል የፖሊሲ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የኢንተርፕራይዞቹን ተወዳዳሪነትና የምርታማነት አቅም ለማጎልበት የፋይናንስ አቅርቦት ሥርዓት ላይ ምቹ ምኅዳር መፍጠር እንደሚገባም ነው ያብራሩት።
አነስተኛ ካፒታል፣ የምርት ቴክኒክ ዘመናዊነት እና ሕጋዊ ጥበቃ አለመኖር ለኢንተርፕራይዝ ልማት ተግዳሮቶች እየሆኑባቸው እንደሚገኝ አንስተዋል።
ሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች የኢኮኖሚ ተዋናይ ብቻ ሳይሆኑ የአይበገሬነት ተምሳሌት የማህበረሰብ ምሰሶ መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
የዛሬው መድረክ ዓላማ የዘርፉን ተግዳሮቶች መለየት፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት እና ተለዋዋጭ የሙያ ህጋዊ ጥበቃ እንዲኖር ከፖሊሲ አውጪዎች ጋር ለመስራት ነው ብለዋል።
ዘርፉን መደገፍ ለገቢ መጨመር እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
መደበኛ ባልሆነው ኢኮኖሚ ውስጥ ያሉ ሀገር በቀል ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በመረዳት በፖሊሲ መደገፍ እንደሚገባም አመላክተዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
