የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ…
የአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ በኢኮኖሚ እና ምርታማነትን በማሳደግ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ያደረገ ተግባር ነው።



በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፋኖሴ መኮንን እንዳሉት÷ የአረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በመጨመር ረገድ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
በዚህም የካርበን ልቀትን በመቀነስ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤትና ለዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ከመዋጋት አንጻር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡
መንግስት ለጉዳዩ ያሳየው ቁርጠኝነትና በመርሐ ግብሩ የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያላት ተጽዕኖ እንዲጨምር እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
በሌሎች ሀገራት መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሽፋን እያገኘ እና ልምድ በመውሰድ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።
የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው ጌትዬ ትርፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ አሁን ላይ የዓለም ፈተና መሆኑን ጠቁመው÷ በርካታ አሉታዊ ጫናዎች እያሳደረ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
ይህንን ፈተና ለመጋፈጥ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበችው ውጤት ብሎም ለአየር ንብረት ለውጥ የሰጠችው ትኩረት የሚበረታታ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤት ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም በስፋት ማስተዋወቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
መርሐ ግብሩን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅበትም ምሁራኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
