Trendings

የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ…

Spread the love

የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ ያደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ…

‎

‎የአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ በኢኮኖሚ እና ምርታማነትን በማሳደግ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ያደረገ ተግባር ነው።

‎

‎በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፋኖሴ መኮንን እንዳሉት÷ የአረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በመጨመር ረገድ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

‎

‎በዚህም የካርበን ልቀትን በመቀነስ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤትና ለዓለም ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ከመዋጋት አንጻር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

‎

‎መንግስት ለጉዳዩ ያሳየው ቁርጠኝነትና በመርሐ ግብሩ የተገኘው ውጤት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያላት ተጽዕኖ እንዲጨምር እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

‎

‎በሌሎች ሀገራት መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሽፋን እያገኘ እና ልምድ በመውሰድ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

‎

‎የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተመራማሪው ጌትዬ ትርፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአየር ንብረት ለውጥ አሁን ላይ የዓለም ፈተና መሆኑን ጠቁመው÷ በርካታ አሉታዊ ጫናዎች እያሳደረ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

‎

‎ይህንን ፈተና ለመጋፈጥ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበችው ውጤት ብሎም ለአየር ንብረት ለውጥ የሰጠችው ትኩረት የሚበረታታ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

‎

‎የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤት ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም በስፋት ማስተዋወቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

‎

‎መርሐ ግብሩን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ዜጋ በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅበትም ምሁራኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *