የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ማሻሻያን ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል – ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)

ለመንግስት ሠራተኛው የተደረገውን የደመወዝ ማሻሻያ ተከትሎ በምርትና አገልግሎቶች ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።
ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ መወሰኑ ይታወቃል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፤ በምርትና አገልግሎት ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ በሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ውስጥ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
በነፃ ንግድ ሥርዓት ስም በምርት ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ መጨመርም ሆነ ማከማቸት አስተዳደራዊና ህጋዊ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ለመንግሥት ሠራተኞች የተደረገውን የደመወዝ ማሻሻያ ተከትሎ ገቢ የሆነ ኢኮኖሚያዊ መንስኤ የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ እርምጃ እንደሚወሰድ አስገንዝበዋል።
የደመወዝ ጭማሪን ሰበብ በማድረግ በምርትና አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ ሁኔታዎችን ካለማጤን የሚመነጭ መሆኑንም ገልጸዋል።
በእስካሁኑ ሂደት የተስተዋለ ነገር የለም ያሉት ሚኒስትሩ፤ ኢ-ምክንያታዊ የምርት ዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ወደ ተሟላ ትግበራ በገባው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የዋጋ ንረትን የማረጋጋትና ገበያን የመምራት ስኬቶችን በመቀመር በሁሉም መስክ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ ለሕግ ተገዥ በመሆን ሀገሩንና ወገኑን ማገልገል እንደሚጠበቅበትም ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
