የቴፒ ግሪን ኮፊ እስቴት ስራ ዕንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ

Spread the love

የቴፒ ግሪን ኮፊ እስቴት ስራ ዕንቅስቃሴ ላይ ትኩረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢኮኖሚ ምሰሶ የሆነውን የቴፒ ግሪን ኮፊ እስቴትን ስራ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለመ የባለድርሻ አካላት ውይይት በቴፒ ከተማ ተካሄደ።

በመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣ በእስቴቱ ባለቤት፣ እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች የተካሄደው ይህ መድረክ፣ ለተቋሙ ስኬት የጋራ ኃላፊነት ለመውሰድ ቃል የተገባበት ሆኗል።

የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ የቴፒ ግሪን ኮፊ እስቴት የሀገር ሀብት መሆኑንና መንግስት ለስኬቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፡ ይህ ድርጅት የበለጠ ውጤታማ ሆኖ ለሀገርና ለህዝብ እንዲጠቅም የሁላችንም ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል። በእርሻው ላይ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችና ብልሹ አሰራሮችን ህብረተሰቡ በንቃት ሊታገል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ማስረሻ በላቸዉ፡ የኢንዱስትሪ ሰላምን በማረጋገጥ ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተቋማትን መደገፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን በውይይት ፈተን፣ የቡና ምርት ጥራቱን ጠብቆ እንዲቀጥል በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።

የቴፒ ግሪን ኮፊ እስቴት ባለቤት ኢንጂነር ታደሰ አድማሱ በበኩላቸው፣ ተቋሙን ከማህበረሰቡ ጋር በማስተሳሰር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከህብረተሰቡ የሚነሱ የማህበራዊ አገልግሎት ጥያቄዎችን በውይይትና በመግባባት እንመልሳለን ብለዋል።

ብልሹ አሰራሮችን ለመቆጣጠር በቴክኖሎጂ የታገዘ የሪፎርም ስራ ጀምረናል ስሉ ገልጸዋል።

ይህ ተቋም ታሪካዊ የሀገር ሀብት ነው፤ በጋራ እንጠብቀው፣ በጋራ እናሳድገው ስሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በተቋሙ ሪፎርም ሂደት የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ፣ በውይይት ላይ የተመሰረተ ሳይንሳዊ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን ስሉም ጠቅሰዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የቴፒ ከተማና የየኪ ወረዳ ነዋሪዎች፣ መድረኩ መዘጋጀቱን አድነቅዉ በእንዲህ ዓይነት ገንቢ ውይይቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና ድርጅቱ የማህበራዊ አገልግሎት ተደራሽነቱን እንዲያሰፋ ጠይቀዋል።

በድርጅቱ ሰራተኞች የሚነሱ የመብት ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች በህግ አግባብ እንዲፈቱ አሳስበዋል።

የእርሻው ውጤታማነትና ትርፋማነት የኛም ስኬት ነዉ ያሉት ተሳታፊዎች ህብረተሰቡን በማስተባበር የሰላም ዘብ በመሆን ኃላፊነታችንን እንወጣለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ፣ የተገኘውን ሰላም በማስቀጠል ድርጅቱ የተሻለ ስራ እንዲሰራ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

መድረኩ በመንግስት፣ በባለሀብቱ እና በህብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን የሶስትዮሽ አጋርነት በማጠናከር፣ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት አቅም የሚሆን መድረክ ሆኖ ተጠናቋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *