አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ የግብርና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነዉ፦አቶ ማስረሻ በላቸዉ



በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሀገር ዓቀፍ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊስ የማስተዋወቅ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ እንደገለጹት፤ የለውጡ መንግስት በግብርና ዘርፍ የተለያዩ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ በግብርና ክፈለ ኢኮኖሚ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በሀገርና በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል።
ግብርና ሰፊዉ የሀገሪቱ ህዝብ መተዳደሪያ እንዲሆን፣የምግብ ዋስትና እና ምግብ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ፣ተኪ ምርት ማምረት፣ኤክስፖርት ምርት በማምረት የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት እንዲሁም ግብርናን በሀገር እና በቤተሰብ ደረጃ በማምረት የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አቶ ማስረሻ በላቸው ጠቁመዋል።
አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ በግብርና ዘርፍ ለምርትና ምርታማነት ማነቆ ሊሆኑ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በሚቀርፍ መልኩ እንደአዲስ ተሻሽለው መቅረቡንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።
ፖሊሲው ለግብርናው ዘርፍ የሚኖረው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ከግንዛቤ በማስገባት በየደረጃው የሚገኙ ሁሉ በፖሊሲዉ የጋራ አረዳድ በመያዝ ለተፈጻሚነቱ በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣የግብርና ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ኢፋ ሙልጌታን ጨምሮ የፌደራል፣የክልሉ አስተባባሪ አካላትና የቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የዞን አስተዳዳሪዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነዉ።
በፍቅር ከበደ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
