ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ያላትን እምቅ ሃብት በማልማት ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማስተሳሰር እየሰራች ነው

Spread the love

ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ያላትን እምቅ ሃብት በማልማት ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማስተሳሰር እየሰራች ነው

ኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል ያላትን እምቅ ሃብት በማልማት ምስራቅ አፍሪካን በኤሌክትሪክ አቅርቦት ለማስተሳሰር እየሰራች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ባለፈ ሌሎች አገራትን በኤሌክትሪክ ኃይል በማስተሳሰር የአፍሪካ የሃይል ቋት ለመሆን ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት ያላትን የተፈጥሮ ሃብት ጥቅም ላይ እያዋለች ትገኛለች፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፥ኢትዮጵያ በሃይል አቅርቦት እያከናወነቻቸው ያሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ከቀጣናው ባለፈ ሌሎች ሀገራትን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ እምቅ የውሃ፣የንፋስና የፀሐይ ተፈጥሮ ሃብቶች የኤሌክትሪክ ሃይል ለማልማት፣ ለማመንጨትና ለማሰራጨት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥሩ ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ በተለይም ባለፉት አምስት አመታት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ለማሳደግ ያከናወነቻቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት።

እየተካሔዱ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ ኃይል በማገናኘት ቀዳሚውን ስፍራ እንድትይዝ ያደርጋታል ብለዋል።

የህዳሴ ግድብን ጨምሮ እየተከናወኑ የሚገኙ የታዳሽ ኃይል ልማት ስራዎች ከራሷ አልፎ ጎረቤት አገራትን ለማስተሳሰር የጀመረችውን ጥረት የሚያፋጥኑ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያገናኙ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ትኩረት ሰጥታ መስራቷ ሁሉንም አካላት ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ለኬንያ፣ለጂቡቲ፣ ለሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ከመሸጥ ባለፈ በዘርፉ ሌሎች ሃገራትን ለማስተሳሰር የያዘችውን እቅድ ለማሳካት አበክራ እየሰራች እንደምትገኝ አስታውቀዋል።

ለጎረቤት ሀገራት ተደራሽ የሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል በአገራቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በመንገድና በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ቀጣናውን ለማስተሳሰር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *