ማኅበረሰቡ የማንነት መገለጫ የኾኑ ማህበራዊ ድልብ ሀብቶችን በመጠበቅ ለሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት እንደሚገባ ተገለጸ።
ማኅበረሰቡ የማንነት መገለጫ የኾኑ ማህበራዊ ድልብ ሀብቶችን በመጠበቅ ለሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጸዋል።




የ2018 የዳውሮ ብሄር የዘመን መለወጫ ቶኪ በዓ የፓናል ውይይት በታርጫ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በፓናል ውይይቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ማኅበረሰቡ የማንነት መገለጫ የኾኑ ማህበራዊ ድልብ ሀብቶችን በመጠበቅ ለሁለንተናዊ ለውጥ መትጋት እንደሚገባም ነው የገለጹት።
በሀገራት የስልጣን ታሪክ ውስጥ የማኅበረሰብ ሀብቶች ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ቶኪ በአን በተገቢው በማልማት ለሁለንተናዊ ዕድገት ማዋል ይገባል ብለዋል።
አውደ ጥናት በበዓሉ አከባበር እና ታሪካዊ ዳራ ላይ የሚነሱ ብዥታዎችን በማጥራት በበዓሉ ጠቀሜታና አከባበር ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ የሚረዳ መኾኑንም ተናግረዋል።
በተዛባ መልኩ በበዓሉ አከባበር ላይ የሚነሱ አሉታዊ አስተሳሰቦችን መመከት እንደሚገባ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ማኅብረሰቡ የራሱ የኾኑ የማህበራዊ ሀብቶችን መንከባከብና መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ የ2018 ቶኪ በአን በማስመልከት በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ እንደገለጹት ከኢፌዲሪ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ቶኪ በዓን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የጥናትና ስነድ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዞኑን ባህልና ታሪክ በማልማት ለአለም ለማስተዋወቅ ያለመ የልማት እና የአንድነት ኮንፈረንስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መከናወኑን የገለጹት አቶ ዳዊት በዚህም ለተግባሩ ስኬት አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሥግነዋል።
የህዝብ የልማት አቅሞችን በማቀናጀት፥ የብሄረሰቡ ተወላጆች በዞኑ ልማትና ሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መኾኑንም ነው ዳዊት የገለጹት።
አቶ ዳዊት አክለው፥ የቶኪ በዓ ዕሴት የኾኑ የልማትና ዕድገት እንዲሁም አብሮነትና አንድነትን በማጉላት ለዞኑ ሁለንተናዊ ለውጥ በጋራ መቆም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
