በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል – አቶ የሺዋስ ዓለሙ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ አስታወቁ።

ኃላፊው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ በክልሉ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት እያንዳንዳቸው በተሰጣቸው ስያሜና መንፈስ መሰረት በታላቅ ድምቀትና ህዝባዊ ተሳትፎ ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል።
እየተጠናቀቀ ያለው 2017 ዓ.ም እንደ ሀገር አበረታች ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደነበር የጠቆሙት አቶ የሺዋስ፣ በተለይ በክልሉ በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች በተሰሩ በርካታ ስራዎች የማንሰራራት ምዕራፍ የታየበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል።
“መጪውን አዲስ ዓመት የምንቀበለው ለስኬት ያበቁንን ጠንካራ ጎኖቻችንን ይበልጥ በማጎልበትና ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በመገምገም ለላቀ ድል የሚያነሳሱን መሰረቶችን በምናጠናክርበት መንገድ ነው” ብለዋል።
የጳጉሜ ቀናት መርሃ ግብር ዋነኛ ዓላማም ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራትን መገምገም፣ የታዩ ለውጦችን ቀጣይነት ማረጋገጥ እና ህብረተሰቡ በልማት ስራዎች ላይ ያለውን ንቁ ተሳትፎ ይበልጥ ማጠናከር መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዚህም መሰረት በክልሉ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት “እመርታና ማንሰራራት” በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበሩ ተናግረዋል።
በ2017 ዓ.ም የጳጉሜ ቀናት የተሰጣቸውን ስያሜዎች ሲያብራሩም፦
ጳጉሜን 1፡ የጽናት ቀን
ጳጉሜን 2፡ የህብር ቀን
ጳጉሜን 3፡ የእምርታ ቀን
ጳጉሜን 4፡ የማንሰራራት ቀን እና
ጳጉሜን 5፡ የነገው ቀን በሚል ስያሜ እንደሚከበሩ አስረድተዋል።
ቀናቱ በተሰጣቸው ስያሜና ጭብጥ መሰረት በተለያዩ የውይይት መድረኮች፣ በጎ ፈቃድ ስራዎችና ሌሎች ህዝብን ባሳተፉ ዝግጅቶች እንደሚከበሩም ኃላፊው አክለዋል።
በመጨረሻም አምስቱ የጳጉሜ ቀናት መርሃ ግብሮች የተሳኩ እንዲሆኑ ሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የመንግስት ሠራተኞችና መላው የክልሉ ህዝብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
