ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ለቶኪ በአ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ለዳውሮ ብሄር የዘመን መለወጫ (ቶኪ-በአ) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ክልሉ የበርካታ ብሄረሰቦች መኖሪያ፣ የብዝሀ ማንነት መገለጫ ኅብረ ብሄራዊ ክልል እንደሆነ በመግለጫው የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ከእነዚህም ውስጥ ቶኪ በአ አንዱ መኾኑን ጠቁመዋል።
የቶኪ በአ በዓል በዳውሮ ብሄር ዘንድ የሠላም፣ የእርቅ፣ የጥጋብ እና የአንድነት መገለጫ መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የበዓሉ ታሪክና ትውፊት ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስተላለፍ መቆየቱን ተናግረዋል።
በቶኪ በአ ስላለፈው አመት ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት፤ መጪው አመት ደግሞ የጥጋብ እና የበረከት እንዲሆን መሠረት የሚጣልበት የምስጋና በዓል መኾኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የጠቆሙት።
በቶኪ በዓ የመጪው አዝመራው ፍሬ እንዲሰጥ፣ ጥጋብ እንዲሆን፣ከጫፍ እስከ ጫፍ ደስታ፣ ፍቅር እና ሠላም እንዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች ለአገር ሠላም እና ዕድገት እጃቸውን ከፍ አድርገው ፈጣሪን የሚማጸኑበት በዓል እንደሆነም ነው ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ የገለጹት።
የበዓሉ እና የባህሉ ባለቤት የሆነው ህዝብ በአደባባይ በመውጣት በዓሉን ሲያከብር ከጊዜ ወደ ጊዜ ህዝባዊነቱ ይበልጥ እየሰፋ መምጣቱንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የጠቆሙት።
በዓሉ ህዝባዊ መሠረቱን ይዞ ፤ ባህላዊነቱንና ትውፊቱን ሳይለቅ እንዲከበር በየደረጃው እየተከበረ መምጣቱ የሚበረታታ መኾኑንም ነው ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ የገለጹት።
በመጨረሻም በዓሉ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን አስተላልፈዋል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
