ለዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቶኪ-ቤዓ” በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን:-አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ “ቶኪ ቤዓ” በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ አመልዕክት አስተላልፏል።
“ቶኪ ቤዓ ” የጥንት አባቶች የስልጣኔና ባህላዊ የዘመን አቆጣጠር ማሳያ፣ በተለያዩ ባህላዊና ትውፊታዊ ክዋኔዎች የሚከበር የዳውሮ ብሔር ዘመን መለወጫ በአውሮጌው ዓመት መጨረሻ እና በአዲሱ ዓመት መቀበያ የሚከበር ውብ ባህልና ዕሴት ስሉ ጠቅሰዋል።
በአሮጌው ዓመት ከቤተሰብ አባላት ጀምሮ ሀገራቸውንና መላው ዓለምን በሰላም ስላከረማቸው ፈጣሪያቸው ምስጋና የሚያቀርቡበት እንደሁም መጪው አዲስ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልጽግናና የምርታማነት ዘመን እንዲሆንላቸው በጋራ ተሰባስበው ለፈጣሪያቸው መልካም ምኞታቸውን የሚያቀርቡበት በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
ቶክ ቤዓ የሀገረሰብ እውቀቶች እና የተደመረ ጥበባትን ያቀናጀ ፣ የስራ ባህልን የሚያበረታታ፣ አትረፍርፎ ማምረትንና ጠግቦ መብላትን፣ ጤናማ ማህበራዊ ግንኙነት ሚዛን የሚያስጠብቅ፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት እንዲሁም መልካም እሴቶችን በሀገር በቀል ቅኝት ያቆየ የዘመን መለወጫ በዓል ነው ስሉም ጠቅሰዋል፡፡
እነዚህ ባህላዊ እሴቶቻችን የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነትና የአብሮነት እሴቶችን የሚያጠናክሩ ለዲሞክረሲ ስርዓት ግንባታና ለሰላም ግንባታ አይተኬ ሚና እንዳላቸው የገለጹት አቶ ፍቅሬ ትውልዱ ሊጠብቀው፣ ሊተገብረውና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳይበረዝ ሊያስተላልፈው ይገባል ብለዋል።
ፓርቲያችን ብልጽግና የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ባህላቸውንና እሴቶቻቸውን በአደባባይ ወጥተው እንዲያከብሩ የራሳቸውን ቋንቋ የመጠቀምና የማሳደግ፣ የራሳቸውን ባህል የመግለጽና የማሳወቅ እንዲሁም ታሪካቸውን የመጠበቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ ምቹ እድል ፈጥሯል።
ባህላዊ እሴቶችን፣ ቋንቋና ሀገር በቀል ዕውቀቶችን የማልማት፣ የመጠበቅ፣ የማስተዋወቅና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ብልጽግና ፓርቲ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
እንኳን ለዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ “ለቶኪ-ቤዓ” በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !!
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
