በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን ነገ ይጀምራል

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን ነገ ይጀምራል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሚገኙ ሁሉም አካባቢዎች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት ነገ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ እንደሚጀመር የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

አቶ አልማው ዘውዴ እንደገለጹት፣ የትምህርት ዘመኑን ስኬታማ ለማድረግ በክረምት ወራት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል።

በዝግጅቱ ወቅት ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ ከማድረግ ጀምሮ፣ ለመምህራንና ለርዕሰ መምህራን የተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና የዘንድሮውን የትምህርት ሂደት ጥራት ያለው ለማድረግ ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖረው አቶ አልማው አብራርተዋል።

በመሆኑም ሁሉም መምህራንና ተማሪዎች ነገ ጠዋት በትምህርት ገበታቸው ላይ ተገኝተው በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ትምህርት እንዲጀምሩ ቢሮው ጥሪውን አስተላልፏል ሲል ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ወላጆችም ልጆቻችሁን በወቅቱ ወደ ትምህርት ቤት በመላክና አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ሲሉ አቶ አልማው ዘውዴ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *