የቦንጋ ከተማ የኮርደር ልማት ሥራ በተሻለ አፈጻጸም እየተከናወነ መኾኑ ተመላከተ።

Spread the love

የቦንጋ ከተማ የኮርደር ልማት ሥራ በተሻለ አፈጻጸም እየተከናወነ መኾኑ ተመላከተ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ የቦንጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመኾን በሁለተኛው ምዕራፍ በቦንጋ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በከተማው እየተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮርደር ልማት ሥራ አፈጻጸም አመርቂ መኾኑን ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራው ከመጀመሪያው ምዕራፍ ተሞክሮ በመቀመር በተሻለ አፈጻጸም እየተከናወነ መኾኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድር፥ የልማት ሥራው ከከተማ ውብት ባሻገር ለበርካቶች የሥራ ዕድል የፈጠረ እንደሆነም አንስተዋል።

ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀባቸውን አከባቢዎችን በማጽዳት ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደሚገባ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ ከመሬት አቀማመጥ አኳያ ትኩረት በሚሹ ቦታዎች በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሁለተኛው ምዕራፍ የኮርደር ልማት ሥራው አጠቃላይ 2.34 ኪሎሜትር የሚሸፍን መኾኑን የገለጹት የቦንጋ ከተማ ስራ-አስኪያጅ አቶ በረከት ወልዴ አጠቃላይ የሲቪል ስራው 75 ከመቶ መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ቀሪ አነስተኛ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድይ እና የስማርት ፖሎች ተከላን ጨምሮ አጠቃላይ ወጪው ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር እንደሚልቅ የገለጹት አቶ በረከት በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚኾን አስረድተዋል።

የሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራው የቦንጋ ከተማን ገጽታ በእጅጉ የቀየረ መኾኑም በጉብኝቱ ተመላክቷል።

በዕድገቱ በዛብህ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *