ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያን የሀገርን ዳር ድንበር እና ክብሯን ለማሰጠበቅ የደም ዋጋ የከፈሉበት የነፃነት ዓርማችን ነው ፦ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ

Spread the love

“ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት

፣ብሔራዊ አንድነታችን፣ሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ”በምል መሪ ቃል ለ18ተኛ ዙር በዞን ማዕከል ታርጫ ከተማ በድምቀት ተከብሯል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያን የሀገር ዳር ድንበር እና ክብሩዋን ለማስጠበቅ የደም ዋጋ የተከፈለበት የነፃነት ዓርማችን ነው ብለዋል።

አክለውም ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያዊያን የማንነት መገለጫ እና ብሔራዊ መግባባታችን የፀናበት እንደሆነም ተናግረዋል።

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጎሉበት ሀገራዊ አንድነትንና ህብረ ብሔራዊ መግባባት የሚፈጠርበት መሆኑንም አመላክተዋል።

የዘንድሮ ማለትም የ18ተኛ ዙር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን ልዩ የሚያደረገው የዳግም አድዋ ድል ተምሳሊታችን የሆነው የህዳሴ ግድባችን የተጠናቀቄበት ማግስት መሆኑ ነው ብለዋል።

በዓሉ በፖሊስ ትርዕት እና በተለያዩ ኩኔቶች ታጅቦ በድምቀት ተከብሯል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር መረሃ ግብሩ ተጠናቋል።

በመረሃ ግብሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ-ጉባኤን የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የዞን ሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ሲል የዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *